South Ethiopia Regional State
የጠበላ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት ዩኒት ኮንስትራክሸን ማቴሪያል (ስሚንቶ፣ ቆርቆሮ፣ ሚስማር ወዘተ)፣ የማዕድን ውጤት/ግብዓት (ድንጋይ፣ አሸዋ፣ ጠጠር)፣ የደን ውጤት (ባህር ዛፍ እንጨት)፣ ኤሌክትሮኒክስ (ኮምፒተር፣ ፕሪንተር ወዘተ)፣ ጽ/መሳሪያ (ኮፒ ወረቀት እስኪርቢቶ ወዘተ)፣ የመኪና ጎማ፣ ሞተር ሳይክልና የመኪና መለዋወጫ ዕቃ፣ የመኪና ሠርቪስ እና ፈርኒቸር በጨረታ አወዳድሮ መግዛ
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 01/2019
በዚህ ጨረታ የሚሳተፉ ተጫራቾች ጨረታውን የሚያቀርበው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በወላይታ ዞን የጠበላ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለጠበላ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ በ2019 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች ኮንስትራክሸን ማቴሪያል (ስሚንቶ፣ ቆርቆሮ፣ ሚስማር ወዘተ) የማዕድን ውጤት/ግብዓት (ድንጋይ፣ አሸዋ፣ ጠጠር) የደን ውጤት (ባህር ዛፍ እንጨት) ኤሌክትሮኒክስ (ኮምፒተር፣ ፕሪንተር ወዘተ) ጽ/መሳሪያ (ኮፒ ወረቀት እስኪርቢቶ ወዘተ) የመኪና ጎማ፣ሞተር ሳይክል እና የመኪና መለዋወጫ ዕቃ የመኪና ሠርቭስ እና ፈርኒቸር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና በሚመለከተው አካል ድርጅታቸው የተመዘገበ ሆኖ የዘመኑን ግብር አጠናቅቆ የከፈሉና ሌሎች ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከዋናው ጋር ተገናዝቦ መቅረብ አለባቸው።
- አቅራቢነት/ በኦንላይን e-GP በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ።
- ተጫራቾች መጨረቻውን መወዳደሪያ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብቻ ለጠበላ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ የከፈሉትን ደረሰኝ ኦርጅናል ይዘው ከግዥ ንብረት አስተዳደር ሥራ ሂደት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከባንክ CPO/ካሽ/ 30,000 ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ማቅረቢያ ሰነድ ሲዘጋጅ በቀረበው ዕቃዎች ዝርዝር መሰረት ሰነዳቸውን ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ኦርጅናሉን፣ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ኦርጅናሉን በተለያየ ሦስት ፖስታ ለየብቻ በታሸገ ኤንቬሎፕ ውስጥ ሆኖ CPOን ጨምሮ ሦስቱንም በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ታሽጎ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ድረስ በጠበላ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በመቅረብ ህንፃ 3 ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ር ሥራ ሂደት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መክተት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከ15 ተከታታይ የሥራ ቀን ድረስ የጨረታ ሳጥን ክፍት ቆይቶ በ15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ የመ/ቤቱ ጨረታ ኮሚቴ አባላትና የመ/ቤቱ ተወካዮች በተገኙበት ከሰዓት 8፡30 ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት /ግለሰብ/ ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7 ቀናት ውስጥ ከመ/ቤቱ ጋር የውል ስምምነት ይፈጽማል።
- ዕቃ /ንብረት ማራገፊያ ቦታ በጠበላ ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ ይሆናል።
- ሁለቱም ወገኖች ውሉን ተግባራዊ ለማድረግ የማይቀርቡበት ሁኔታ ቢከሰት የኢት/ያ ፍትሐ ብሔር ሕግ በሚያዘው መሠረት የሚፈፀም ሲሆን ሌሎች በውሉ አፈፃፀም መሠረት አስፈላጊ መብትና ግዴታዎችን የሚያካትት ይሆናል።
- ማንኛውም ግዥ የሚፈፀመው በነጠላ ዋጋ ይሆናል።
- በጨረታው ዝቅተኛ ዋጋ አቅርበው ያሸነፈ አሸናፊ ውል ለመግባት ፈቃደኛ ካልሆነ በሁለተኛ ደረጃ ያሸነፈው በመጀመሪያው ዝቅተኛ ዋጋ ለማቅረብ ፈቃደኛ ከሆነ ማቅረብ ይችላል።
- የከተማው ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡-0940318347/0910796224
በደቡብ ኢ/ክ/ መንግስት በወላይታ ዞን የጠበላ ከተማ
አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት ዩኒት
Tender details
- Deadline: 2026-08-18
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-18 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: የወላይታ ዞን የጠበላ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ዩኒት
- Bid bond: 30,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 04, 2026)
- Posted at: 2026-08-04T12:01:36.000Z