Building and Finishing Materials
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የሀገራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ማቴሪያሎዎቹን በሀገራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት1፡-የህንፃ መሣሪያ ግዥ
- ሎት2፡- የጽሕፈት መሣሪያ ግዥ
- ሎት3:- የቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ግዥ፤
- ሎት4:- የኤልክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ፣
- ሎት5:- የሞተርና መለዋወጫ ግዥ
- ሎት6:- የጀነሬተር ግዥ
- ሎት7፡- የመኪና ጎማ ግዥ፤
- ሎት8፡- አሸዋ በቢያጆ፣ ጠጠር 02 በማሽን የተፈጨ በቢያጆ፤ የፍልጥ ድንጋይ በቢያጆ የሙሊት ድንጋይ በቢያጆ ብሎኬት ባለ-10 ብሎኬት ባለ-15 በሎኬት ባለ-20
- ሎት9፡-የሴክተር መ/ቤቶች መኪኖች ጥገና ጉልበት ዋጋ እና መለዋወጫ እቃዎች ግዥ፤- አምቡላንስ መኪና ታርጋ-04266 የላንድ ኩሩዘር መኪና ታርጋ-30793፤የቀይ መስቀል መኪና ታርጋ-02337 እና ፓትሮል መኪና ታርጋ-0401 ጥገና ማድረግ፤
ስለሆነ በጨረታው ለመሳተፊ የሚፈልግ ሁሉ ተሻሽለው በወጣው በመንግስት ግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 70/2017 ዓ/ም መሰረት፡-
1. የ2019 ዓ/ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤
2. የዘመነ ግብር የከፈለበት መረጃ ማቅረብ የሚችል፤
3. የግብር ከፋይነት ምዝገባ ቁጥር Tin Number/ያላቸው
4. የቫት ተመዝጋቢ የሆነበት መረጃ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፤
5. ከሽያጭ ዋጋ ላይ ለመንግስት ግብር 3% ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ፤
6. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
7. የዕቃ አቅራቢነት በኦንላይን የተመዘገበበትን ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
8. የጨረታ ሁኔታ በአይቴም ወይም በጥቅልል ሊሆን ይችላል፤
9. የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በመለየት ኦርጂናሉንና ኮፒውን የጨረታ ሰነድ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በማስገባት በሴም በታሽገው እምቨሎፕ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በቁጫ አልፋ ወረዳ/ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ-5 ላይ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፤
10. በጨረታ ሂደት ላይ አሸናፍ የሆነ ድርጅት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ የውል ማስከበሪ 25% ማስያዝ ግደታ አለባቸው ፤
11. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል።
12. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ የማይመለስ 400/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ወደ ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋ/ፕ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቀጥር 5 ድረስ በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰነድ መግዛት የሚችሉ ይሆናሉ።
13. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተረጋገጠ ህጋዊ CPO እና በጥሬ ግንዘብ ከሚሳተፉበት 25,000/ ሃያ አምስት ሺህ ብር/ ብቻ ጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ግደታ አለባቸው ፤
14. የጨረታ ሣጥን የሚታሽገው የጨረታ ማብቂያ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 10:00 ሣዓት ይሆናል፤
15. ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን ከጧቱ 4:00 ሣዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤
16. በጨረታው አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ ዕቃውን እስከ ቁጫ አልፋ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ድረስ የጫኚ አውራጂ እና የጭነት ወጪን በመሸን ማቅረብ ይኖርባቸዋል ።
17. ተጫራቾች ወይም የጨረታ ወኪል ያለመገኘት ጨረታውን መክፈት አያስተጓጓልም፤
18. የ16ኛው ቀን ሰንበት ወይም በዓል ከሆነ በቀጣይ ስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፤
ማሳሰቢያ፡-
በጨረታው አሸናፍ ድርጅት ወይም ግለሰብ የዕቃው ከጥራትና ደረጃ ዝቅ ብል፣ ዕቃው ቢጎድል ከተዋወለው ከውሉ ጊዜው ቢያልፉ በህግ መሰረት ለመንግስት ከገባሁት ከጠቅላላ ውል ገንዘብ ላይ 25% ያህሉን የሚደርሰውን ብር ተቀጥቼ ገንዘብ ተመላሽ ለማድረግ በፍ/ህ/ቁጥር 3132 መሰረት የፀና ይሆናል ።
ጽ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ መረጃ ስልክ፦ 0921 906 270 /0976 135 648/ 0984 666 189 ደውለው ይጠይቁ።
በጋሞ/ዞን/ቁጫ/አልፋ/ወ/ፋ/ን/ል/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-06
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 10:00
- Bid opening: 2026-10-07 10:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጧቱ 4:00
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Gamo Zone Kucha Alfa Woreda FEDB
- Bid bond: 25,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 400/ሁለት መቶ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Sep 19, 2026)
- Posted at: 2026-09-19T07:39:50.000Z
- Source: 2merkato