Wood and Wood Working

የጋሞ ዞን ፋይናንስ ፕላን ልማት መምሪያ በዞኑ አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ እና ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ መሀል በደገና ቀበሌ የጉጫ ኮንፓርትመንት ሰው ሰራሽ ደን 8.09 ሄክታር እና 350.5 ሜ/ኩ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጋሞ ዞን ፋይናንስ ፕላን ልማት መምሪያ በዞኑ አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ እና ጨንቻ ዙሪያ ወረዳ መሀል በደገና ቀበሌ የጉጫ ኮንፓርትመንት ሰው ሰራሽ ደን 8.09 ሄክታር እና 350.5 ሜ/ኩ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡-

በዚሁ መሠረት፦

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው።
  2. ማንኛውም ተጫራቾች ከውድድሩ በፊት የደኑን መገኛ ቦታ በራሱ ወጪ አይቶ ነጠላ ዋጋ መሙላት ይኖርበታል።
  3. ተጫራቾች ደኑን ለማንሳት አስፈላጊውን የሰው ሃይልና መሳሪያዎችን በራሳቸው ማቅረብ የሚችሉ
  4. የጨረታ ማስከበሪያ(Bid Security) ለእያንዳንዱ ሎት ብር 120,000(አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት በዋናው የህጋዊነት ሰነድ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የፋይናንሻል ጨረታ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ተሞልቶ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶግራፍከ ኮፒው በተለያዬ ፖስታ ታሽጎ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ እላዩ ላይ ተጽፎበት ፣ በሶስቱም ፖስታዎች ላይ ስም ፣ አድራሻና በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በማሳረፍና በመፈረም እንዲሁም፡- የህጋዊነት ሰነዶችን አንድ ፎቶግራፊክ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ በፖስታ ከላይ በተገለጸው በተመሳሳይ ሁኔታ ታሽጎ ሁሉንም ፖስታዎች በአንድ እናት ፖስታ እላዩ ላይ ማህተም ፣ አድራሻና ስም ጽፎ በመፈረም አሽጎ እስከ 16ኛው ተከታታይ ቀናት 4፡00 ሰዓት ድረስ በጋሞ ዞን ፋይናንስ ፕላን ልማት መምሪያ ግዥና ን/ አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ለዚሁ በተዘጋጅው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘውትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ጨረታው በ16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ልክ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።

ማሳሰቢያ፡-መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስልክ ቁ 046-881-3338 ይደውሉ።

የጋሞ ዞን ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-05
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በ16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-05 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በ16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: የጋሞ ዞን ፋይናንስ ፕላን ልማት መምሪያ
  • Bid bond: 120,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Sep 19, 2026)
  • Posted at: 2026-09-19T08:37:58.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders