South Ethiopia Regional State

በደቡብ ኢ/ክ/ መንግስት በወላይታ ዞን የጠበላ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ዩኒት በጠበላ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በ2019 ዓ/ም ካፒታል በጀት የጠበላ ከተማ በረት ዙሪያ አጥር ግንባታ፣ ኮብልስቶን ንጣፍ እና በጠበላ ከተማ አስተዳደር ጠበላ አጎዳማ ቀበሌ አስተዳደር ቢሮ ግንባታ ቀሪ ሥራ ሙሉ ማቴሪያል በማቅረብ መሥራት የሚችል በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ጨረታ ቁጥር 01/2019

በደቡብ ኢ/ክ/ መንግስት በወላይታ ዞን የጠበላ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ዩኒት በጠበላ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በ2019 ዓ/ም ካፒታል በጀት የጠበላ ከተማ በረት ዙሪያ አጥር ግንባታ : ኮብልስቶን ንጣፍ እና በጠበላ ከተማ አስተዳደር ጠበላ አጎዳማ ቀበሌ አስተዳደር ቢሮ ግንባታ ቀሪ ሥራ ሙሉ ማቴሪያል በማቅረብ መሥራት የሚችል ከዚህ በታች ያለውን መሰፈርት የሚያሟላ ሙያተኛ በጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።

ስለዚህ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና በሚመስከተው አካል ድርጅታቸው የተመዘገብ ሆኖ የዘመኑን ግብር አጠናቅቆ የከፈሉና ሌሎች ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከዋናው ጋር ተገናዝቦ መቅረብ አስባቸው።

  1. የታደሰ ንግድ ፈቃድና ምዝገባ ምስክር ወርቀት ያለዉ።
  2. EGP በኦንላይን በአቅራቢነት የተመዘገበ ደረጃቸዉ GC/BC 7 አና ከዛ በላይ የሆነ።
  3. ተ.እ.ታ (VAT) ፡ የግብር ከፋይ መለያ ቲን ያለዉ።
  4. ዉክልና ደብዳቤ ያለዉ የዘመኑን ዕዳ የከፈለና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል።
  5. አሸናፊ ሚሆነዉ ተጫራች በወቅታዊ የገበያ ዋጋ አማካይ ዉስጥ የገባ ይሆናል።
  6. የጊዜ ሠሌዳ አዘጋጅቶ ማቅረብ የሚችል እና ግንባታዉን ባቀረበዉ ጊዜ መሰረት ማጠናቀቅ የሚችል።
  7. ተጫራቾች መጫረቻዉን |መወዳደሪያ ሠነድ የማይመለስ ብር 1,000 /አንድ ሺህ/ ለጠበላ ከተማ ገቢዎች ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ የከፈሉትን ደረሰኝ ኦርጀናል ይዘዉ ከግዥ ንብረት አስተዳደር ሥራ ሂደት ሠነዱን መዉሰድ ይችላሉ።
  8. ተጫራች ከ2016 ዓ/ም ጀምሮ ያለዉን ጥሩ ሥራ አፈፃፀም ያለዉ ማቅረብ የሚችል።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ኦርጅናል፣ኮፒ 1 እና ኮፒ 2 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በተለያየ 4 ፖስታ ለየብቻ በታሽገ ኤንቬሎፕ ውስጥ ሆኖ CPOን ጨምሮ አራቱንም በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ ታሽጎ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30ኛዉ ቀንና ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በጠበላ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በመቅረብ ህንፃ 3 ግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ር ሥራ ሂደት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል።
  10.  ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ለ30 የሥራ ቀናት የጨረታ ሳጥን ክፍት ቆይቶ በ31ኛዉ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ የመ/ቤቱ ጨረታ ኮሚቴ አባላትና የመ/ቤቱ ተወካዮች በተገኙበት 4፡30 ይከፈታል።
  11. የጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት/ ግለሰብ/ ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ7 ቀናት ውስጥ ከአሠሪ መ/ቤት ጋር የግንባታ ሥራ ውል ስምምነት ይፈጽማል።
  12. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO/ካሽ/ 80,000 ማቅረብ አለባቸው።
  13. አሸናፊ ተጫራች ለዉል ማስከበሪያ 10% ዋስትና ሲፒኦ /CPO ማስያዝ የሚችል።
  14. አሸናፊ ተጫራች 30% የሚጠይቅ ከሆነ ለቅድመ ክፍያ ተመጣጣኝ ዋስትና ሲፒኦ /CPO ማስያዝ የሚችል።
  15. ሁሉቱም ወገኖች ውሉን ተግባራዊ ለማድረግ የማይቀርቡበት ሁኔታ ብከሰት የኢት/ያ ፍትህ ብሐር ሕግ በሚያዘው መሠረት የሚፈፀም ሲሆን ሌሎች በውሉ አፈፃፀም መሠረት አስፈላጊ መብትና ግዴታዎችን የሚያካትት ይሆናል።
  16. በጨረታው ዝቅተኛ ዋጋ አቅርበው ያሸነፈ አሸናፊ ውል ለመግባት ፈቃደኛ ካልሆነ በሁለተኛ ደረጃ ያሸነፈው በመጀመሪያው ዝቅተኛ ዋጋ ለመሥራት ፈቃደኛ ከሆነ መሥራት ይቻላል።
  17. የከተማው ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፍል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

ስልክ /0940318347/0910796224

የወላይታ ዞን  የጠበላ  አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ዩኒት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-08
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ31ኛዉ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-08 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ31ኛዉ ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Tebela City Finance Office
  • Bid bond: 80,000 ብር
  • Bid document price: 1,000 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 04, 2026)
  • Posted at: 2026-08-04T12:14:27.000Z
← Back to all tenders