Disposal, scrap and surplus sales

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ ያገለገሉ ቀላል የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች (Auxillary Equipments) በግልፅ ጨረታ ለመሽጥ ይፈልጋል

Description

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ ያገለገለ ቀላል የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች (Auxiliary Equipment's) በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ የተዘጋጀ ሰነድ

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ ያገለገሉ ቀላል የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች (Auxiliary Equipment's) በግልፅ ጨረታ ለመሽጥ ይፈልጋል። በሽያጭ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተጫራቾች መመሪያ የማክበርና የመፈፀም ግዴታ አለባቸው።

ክፍል አንድ
የተጫራቾች መመሪያ

1. ይህ ጨረታ ድርጅት ወይም ግለሰብ ሊሳተፍበት ይችላል።

2. ተጫራቾች መታወቂያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምሥት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ የሥራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ስዓት ከሰኞ እስከ አርብ የሥራ ቀናት ጠዋት ከ3፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡00 ስዓት ቃሊቲ ግቢ (ቃሊቲ ቶታል አካባቢ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ ግቢ ) በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ።

5. አንድ ተጫራች የተለያዩ ያገለገሉ ቀላል የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች (Auxiliary ዓይነታቸውን መሰረት በማድረግ የሚገዛበትን የአንድ ዋጋ እና ጠቅላላ የሚገዛውን መጠን በማስገባት መሠረት ይኖርበታል።

6. ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በመግለፅ በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ መፈረም አለባቸው።

7. ጨረታው ነሀሴ 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው (በዕለቱ) በ4፡30 (አራት ሰዓት ተኩል) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።

8. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

9. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር የመታወቂያ እና የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ማሳሰቢያ፡-ለሽያጭ የቀረቡት የተለያዩ ያገለገሉ ቀላል የኮንስትራክሽን መሣሪያዎች (Auxiliary Equipment's) እቃዎች ናቸው።

ስልክ ቁጥር 011-440-3434

ማዞሪያ 011-442-2270/71/12

E-MAIL አድራሻ [email protected]  

የድህረ ገፅ አድራሻ WWW.dce-et.com 

ፖሳቁ 341 4 11 440-0471/011 442-0746
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-20
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-20 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Defense Construction Enterprise (DCE)
  • Buyer address: ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
  • Bid document price: 500 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 05, 2026)
  • Posted at: 2026-08-05T07:00:44.000Z
← Back to all tenders