Oromia

የወሊሶ ከተማ ገ/ጽ/ቤት በ2019 የበጀት አመት የሰራተኛ የደንብ ልብሶች፣ የተለያዩ የጽፈት መሳሪያዎችን፣ የመኪና ጎማዎችን፣ ፈርኒቸሮችን፣ የኤሌክትሮንክስ እና ሞተር ሳይክሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር-01/2019

የወሊሶ ከተማ ገ/ጽ/ቤት በ2019 የበጀት አመት የሰረተኛ የደንብ ልብሶች፤ የተለያዩ የጽፈት መሳሪያዎችን የመኪና ጎማዎችን፤ ፈርኒቸሮችን፤ የኤሌክትሮንክስ እና ሞተር ሰይክሎችን የክልሉ መንግስት ባወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ ቁጥር 157/2002 በመከተል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ዝርዝር ሁኔታዎች፡-

ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ተከታታይ የስራ ቀን ድረስ ይሆናል፣ ስለዕቃዎቹ ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፅ ሰነድ በየሎቱ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በሲንቄ ባንክ በወሊሶ ከተማ ገንዘብ ገጽ ቤት በተከፈተው ሒሳብ ቁጥር 1071027311218 በማስገባት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከወሊሶ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

የተጫራቾች ግዴታዎች፡-

1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው።

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት ያለቸው እንዲሁም በፌዴራል ገ/ሚኒስቴር ወይም በኦሮሚያ ገንዘብ ቢሮ ባዘጋጀው የዕቃ እና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው።

4. ተጫራቾች የጨረታ መስከበሪያ ህጋዊ ከሆና ባንከ የተረጋጋ CPO በየሎቱ 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ/ ማስያዝ አለባቸው

5. ተጫራቹ ከማጭበርበር፤ ከሙስና፣ ከማታለልና የማስገደድ ድርግት የማይፈጽሙ መሆኑን ለማረጋገጥ ግዴታ ለመግባት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ የሚገኘውን ቅጽ ሞልተው በመፈረም ማስገባት አለበቸው።

6. አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈርሙ የውል ማስከበሪያ ዋስትና 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ያለ ስርዝ ድልዝ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት በኦርጅናል እና በኮፒ በመለየት በኤንቨሎፕ በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ወሊሶ ከተማ ገ/ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በዝሁ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 8:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወሊሶ ከተማ ሁለገብ አዳራሽ ይከፈታል።

8. ጨረታው የሚከፈትበት ቀኑ በዓል ከሆነ ጨረታው በቀጠዩ ቀን በተመሳሰይ ቦታና ሰዓት ይከፈታል።

9. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኛ ጨረታውን በከፍልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች(011-341-3012 ) በመደወል መረዳት ይችላሉ።

የወሊሶ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት

ወሊሶ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-21
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-21 14:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: የወሊሶ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Bid bond: 30,000.00 ብር በየሎቱ
  • Bid document price: 500.00 ብር በየሎቱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 05, 2026)
  • Posted at: 2026-08-05T07:56:38.000Z
← Back to all tenders