Office furniture
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት አላቂ የጽህፈት ዕቃዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች እና ለጥገና አገልግሎት የሚውሉ የግንባታ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2019
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለቢሮ መገልገያና ለጥገና አገልግሎት
የሚውሉ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ምድብ 1 አላቂ የጽህፈት ዕቃዎች
- ምድብ 2 የጽዳት ዕቃዎች
- ምድብ 3 ለጥገና አገልግሎት የሚውሉ የግንባታ ዕቃዎች
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ።
- በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት ( TIN No) ያላቸው።
- የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና የጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከሀገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት የሚሰጣቸውን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
- በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ግብር ከፋይነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለምድብ 1 ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ)፣ ለምድብ 2 ብር 40,000.00 (አርባ ሺህ)፣ እና ለምድብ 3፡ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ) የጨረታ ማስከበሪ (Bid Bond) ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 26/12/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 602 ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በዚሁ ቀን 26/12/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 602 ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ምድብ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ከድርጅቱ ግዥና ትራንስፖርት ክፍል ቢሮ ቁጥር 11 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ምድብ ናሙና የማቅረብ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-- ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡-011 552 5405/ 011 551 3288
ፖ.ሣ.ቁ 3375 አአ
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት
Tender details
- Deadline: 2026-09-01
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-09-01 10:05
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Petroleum Supply Enterprise
- Buyer address: ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ ስልክ ቁጥር 011-551-3288 ፖ.ሣ.ቁ 3375 አአ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Aug 05, 2026)
- Posted at: 2026-08-05T07:58:51.000Z