Office furniture
በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳደር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የተሽከርካሪ ጎማ እና መለዋጠጫ እቃዎችና የተሽከርካሪ ቅባትና ዘይት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳደር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፤የጽዳት እቃዎች፤የተሽከርካሪ ጎማ እና መለዋጠጫ እቃዎችና የተሸከርካሪ ቅባትና ዘይት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች እንድትሳተፉ ይጋብዛል ።
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው /ያላት/ ፤
- በዘርፉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው /ያላት/
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ በተመሰከረለት ትክክለኛ ሲፒኦ ወይም በህጋዊ ደረሰኝ መሂ-1/፡- ማስያዝ አለባቸው።
|
ሎት |
የጨረታው ዓይነት |
የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና |
|
1. |
የጽህፈት መሳሪያዎች |
300 |
40,000 |
|
2. |
የጽዳት እቃዎች |
100 |
6,000 |
|
3. |
የተሽከርካሪ ጎማ እና መለዋወጫ እቃዎች |
200 |
15,000 |
|
4. |
የተሽከርካሪ ቅባትና ዘይት |
200 |
10,000 |
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ድረስ ባሉት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከላይ የተጠቀሰውን የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ የማይመለስ ብር በመክፈል ከሲ/ዋዩ/ ወ/ገን/ጽ/ቤት ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡10 ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ዋጋ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ካለምንም ስርዝ ድልዝ በመሙላት ኦርጅናሉን ብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በፖስታው ላይ ስማቸውን፣ አድራሻቸውን እና የሚወዳደሩበትን የጨረታ ዓይነት በመፃፍ ሲያ/ዋ/ወ/ገን/ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጪ በማጓጓዝ በፑሉ በሚገኙ ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋል።
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ካሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ከተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር በባንክ በተመሰከረ ትክክለኛ ሲፒኦ ወይም በህጋዊ ደረሰኝ /መሂ-1/ በማስያዝ ውል ይፈጽማል።
- መ/ቤቱ በግዥው ላይ 20% የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው።
- የጨረታ ውድድሩ በጥቅል ዋጋ ላይ የተመሰረተ ነው።
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116 200 679 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-25
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Bid opening: 2026-08-25 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡10
- Region: Amhara
- Publishing entity: Siyadebr & Wayu Woreda FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published on: Addis Zemen (Aug 09, 2026)
- Posted at: 2026-08-10T12:47:11.000Z