Office furniture

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት በወረዳው ላሉ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል 1ኛ ዙር ጥቅል ግዥ ማለትም

1.የጽሕፈት መሣሪያ፣2.የደንብ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ 3. አላቂ የጽዳት ዕቃወች 4.የኤሌክትሮኒክሰ 5.የመኪና ጎማዎች 6.ህትመት 7.መስተንግዶ ውሃና ቆሎ/ 8.የደንብ ልብስ ስፌት 9.የሃገር መኪና ኪራይ 10.ዲኮርና ድንኳን ኪራይ፡11.የኤሌክትሮኒክስ ጥገና እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ከገቢዎች ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ሆነው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

3. የጨረታ ሰነዱን ለአንዱ ሎት የማይመለስ 300(ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህን ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋት 2፡30 – 6፡30 ከሰዓት 7፡30-11፡30 ሰዓት በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት አዲሱ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 203 መግዛት ትችላላችሁ።

4. ተጫራች ከዚህ በታች የተጠቀሰዉን የጨረታ ማሰከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ መቅርብ አለባቸዉ

ሎት ቁጥር

የሎት ዝርዝር

የጨረታ ሰነድን የማይመለስ ብር

የተጠቀሰዉ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በኢትዮጵያ ብር

ሎት1

አላቂ የጽፈት መሳሪዎች

300

27,600

ሎት2

የደንብ ልብስ

300

56,700

ሎት3

ኣላቂ የጽዳት ዕቃዎች

300

45,900

ሎት4

የኤሌትሮኒክስ እቃዎች

300

20,600

ሎት5

የመኪና ጎማዎች

300

10,000

ሎት6

ህትመት

300

12,400

ሎት7

መስተንግዶ

300

6000

ሎት8

የደንብ ልብስ ስፌት

300

3000

ሎት9

የሃገር መኪና ኪራይ

300

6000

ሎት10

ዲኮር ድንኳን እና ጀነሬተር ኪራይ

300

5000

ሎት11

የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች

300

5600

5. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ለእያንዳንዱ ሎቶች ለየብቻ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለጸው መሰረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማስያዝ አለባቸው።ከሲፒኦ ውጭ ምንም አማራጭ የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን።

6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን መሥሪያ ቤቱ በሰጣቸው የአንዱ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ጠቅላላ ዋጋ በሚለው ቦታ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላትና የድርጅታቸውን ማህተም ፊርማና ሙሉ ስም አድራሻቸውን በመግለጽ፤ የቴክኒካልና የፋይናንሽያል ኦርጂናል በአንድ ፖስታ ላይ ኮፒያቸውን ለብቻ በሌላ ፖስታ በማሸግ ባጠቃላይ ለአንድ ሎት ሁለት ፖስታ ብቻ ላይ በማሸግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 203 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።ሁሉንም ሎቶች ለየብቻ አሽገው የማያቀርቡ ተወዳዳሪዎች ከውድድሩ ውጪ ይደረጋሉ።

7. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎች ዓይነት ለመለየት የሚያስችል ናሙና ለተጠየቀባቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው ናሙና ከላቀረቡ ጨረታ መሳተፍ አይችልም ።

8. የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ይታሸጋል በዚሁ ቀን 4፡30 ጨረታው ተጫራቾች | ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። በመሆኑም ከተጠቀሱት ቀንና ሰዓት ውጪ የሚቀርቡ ማንኛውም የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

9. የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት 11 ኛው ቀን በዓል ከሆነ የሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡ 00 ሰዓት ይታሸጋል በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

10. ለጨረታው የሚቀርቡ ዕቃዎች ጥራታቸውንና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው፡፡ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ወጪ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ፋ/ጽ/ቤት ግምጃ ቤት ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል።

11. ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊ ሆነው ከተገኙባቸው ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከጽ/ቤት ጋር የግዥ ውል ስምምነት በመፈራረም ከተፈረመበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 7(ሰባት) የሥራ ቀናት ዕቃዎችን ማስረከብ ይኖርባቸዋል።

12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኝ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ እና 20 % ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአካል በመቅረብ ከመገናኛ ወደ ሰዓሊተ ምህረት ቤ/ክ በሚወስደው መንገድ ጉርድ ሾላ በሻሌ ሆቴል ፊት ለፊት ወይም በስልክ ቁጥር 011-812-24-86 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ።

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-21
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-21 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bole Sub City Woreda 7 Administration Finance and Economic Development Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በየሎቱ 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 09, 2026)
  • Posted at: 2026-08-10T07:39:37.000Z
← Back to all tenders