External audit and assurance

ካለን ብናካፍል የሕፃናት፣ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል: የሂሳብ አዋቂ በጨረታ ለማወዳደር የወጣ ማስታወቂያ

Description

የሂሳብ አዋቂ በጨረታ ለማወዳደር የወጣ ማስታወቂያ

ካለን ብናካፍል የሕፃናት፣ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ማስተዳደሪያ በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት ነሀሴ 17/2014 ዓ.ም በመዝገብ ቁጥር 6368 በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ተመዝግቦ ሕጋዊ ሰውነትን አግኝቷል።

በመሆኑም በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር የ2018 በጀት አመት እንቅስቃሴውን በሙሉ የውጭ ኦዲተር ኦዲት ለማድረግ ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟሉ አካላት ጨረታውን መወዳደር ይችላሉ።

1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ምዝገባና 2 ዓመት እና ከዛ በላይ የስራ ልምድ ያለው።

2. የታደሰ የንግድ ፈቃድ የግብር መለያ ሰርተፍኬት ያለው።

3. ሙያው በሚጠይቀው ጥራት በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰርቶ ማስረከብ የሚችል።

4. የበጀት ዓመቱን ሂሣብ ኦዲት ለማድረግ በሰጠው ጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ የጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ ማስያዝ የሚችሉ።

5. ተጫራቾች ለሚያከናውኑት ተግባር ከድርጅቱ ጋር ዝርዝር ውል ለመፈራረም ፈቃደኛ የሆነ።

6. ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን ጨረታው ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ የሚገልጽ ክሪላንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች ስለመልካም ስራ አፈፃፀማቸው ከአሁን በፊት የሒሳብ ምርመራ (ኦዲት) ካደረጉባቸው ድረጅቶች የተፃፈላቸውን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

8. የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት (ተመዝጋቢ ከሆኑ)፣ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት (ቲን) እና ሌሎች ለጨረታ የሚጠቅሙ ማስረጃዎችን የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።

9. የሂሳብ ምርመራ ወይም (ኦዲት) አዲስ አበባ ከተማ።

1ዐ. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 7 (ሰባት) ቀናት በስራ ሰዓት በድርጅታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመግዛት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክስን ጨምሮ) በመሙላት ኦርጅናሉንና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ ቢሮ ቁጥር 805 ማስገባት ይኖርባቸዋል።

11. ተጫራቾች የበጀት አመቱን አዲት ስራ፣ የኦዲትስራውን የሚከናወንበትና የስራ ዝርዝር እና በመጨረሻ የሚያቀርቡት የኦዲት ሪፖርት ይዘት እንዲሁም የሚወስድባቸውን ግዜ በተመለከተ የድርጊት መርሃ ግብር (ማስኬጃ ውል) በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

12. ጨረታው ለ7 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ8ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 805 ይከፈታል።

13. የጨረታ መክፈቻ 8ኛው ቀን በዓል (የእረፍት ቀን) ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል። በሀገር አቀፍ በዓላት ካልተዘጋ በስተቀር ዘወትር 6፡00 የስራ ሰዓት ሲሆን ይህም እንደ አንድ የስራ ቀን ይቆጠራል።

14. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 13 22 74 78 / 09 41 02 03 04

ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል/ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከተማ ከዘፍመሽ ወደ ሾላመብራት በሚወስደው መንገድ ሲትእስኩየር ሞል ስምንተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 805

ካለን ብናካፍል የሕፃናት፣ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል


Tender details

  • Deadline: 2026-08-12
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ለ7 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ8ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00
  • Bid opening: 2026-08-12 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ለ7 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ8ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kalen Binakafil Humanitarian Association
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 05, 2026)
  • Posted at: 2026-08-05T08:49:20.000Z
← Back to all tenders