Disposal, scrap and surplus sales

ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ግዜያት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ባለመፈጸሙ ምክንያት እና በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ እና በሃራጅ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል

Description

በጉምሩክ ኮሚሽን የአ/አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ልዩ ልዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ እና በሃራጅ ጨረታ ቁጥር 10/2019፡ 11/2019: 12/2019፡ 13/2019፡ 14/2019፡ 15/2019፡ 16/2019 እና 17/2019 የጨረታ ማስታወቂያ፣

ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ግዜያት የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ባለመፈጸሙ ምክንያት እና በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፡ ሞባይሎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ጌጣጌጥ እና አካላት፣ አልባሳት፣ጫማዎች፣ጊርቦክሰ እና ሌሎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ እና በሃራጅ ጨረታ ቁጥር 10/2019 በቀን 4/12/2018 ዓም፣ ጨረታ ቁጥር 11/2019 በቀን 7/12/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 12/2019 በቀን 11/12/2018 ዓም፣ ጨረታ ቁጥር 13/2019 በቀን 14/12/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 14/2019 በቀን 18/12/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 15/2019 በቀን 21/11/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 16/2019 በቀን 25/12/2018 ዓም እና ጨረታ ቁጥር 17/2019 በቀን 28/12/2018 ዓ.ም በመሆኑ የቀጣይ 2019 በጀት ዓመት ዕቅድ በተፈለገው መጠን ለማሳካት ለሁሉም ተደራሽነት ባለው መልኩ በጋዜጣ ማስታወቂያ እንዲወጣልን እየጠየቅን ዝርዝር መረጃ ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 1-14 እንገልፃለን።

በመሆኑም

1. በቅጽ/ቤቱ ለሚካሄደው ጨረታ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የተከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ማንኛውም ግልጽ ጨረታ ተጫራች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ስዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 – 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 - 11:00 እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 – 6:00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ ጉምሩክ መጋዘን ቅጥር ግቢ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላል።

3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ(5%) ዋስትና( CPO) CUSTOMS COMMSSION ADDS ABABA ARPORT CUSTOM BRANCH OFFICE ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ካርጎ መጋዘን እና ገርጂ መጋዘን ነሐሴ 4/2018 ዓም፣ ነሐሴ 7/2018 ዓም፣ ነሐሴ 11/2018ዓ.ም፣ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም፣ ነሐሴ 18/2018 ዓ/ም፣ ነሐሴ 21/2018 ዓም ነሐሴ 25/2018 ዓም፡ ነሐሴ 28/2018 ከቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በቀን በ8፡15 የሚከፈት ይሆናል።

5. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ለጨረታ የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዘው በቀረቡት ቅጾች መሠረት ለመረጡት የዕቃዎች ኮድ የተሰጠ ዋጋ የተጫራቾች ስም አድራሻ፣ ፊርማና የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ(CPO) እና ከላይ በተ.ቁ 1 የተገለጹትን ሰነዶች ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ ላይ በመፈረም አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን መግዣ ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም።

7. ማንኛውም ተጫራች የሰጠውን የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ የጨረታው ውጤት እስከሚታወቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።

8 የጨረታው አሸናፊዎች ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ በ05(አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለባቸው።

9. ከላይ በተ.ቁ 8 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰደ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

  • በተራ ቁጥር 01 – 09 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም በሃራጅ ጨረታ ቁጥር 10/2019
  • በቀን 4/12/2018 ዓም ጨረታ ቁጥር 11/2019 በተን 7/12/2018 ዓም ጨረታ ቁጥር 12/2019
  • በቀን 11/12/2018 ዓም ጨረታ ቁጥ 13/2019 በቀን 14/12/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 14/2019
  • በቀን 18/12/2018 ዓም፣ ጨረታ ቁጥር 15/2019 በቀን 21/12/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 16/2019
  • በቀን 25/12/2018 ዓም ጨረታ ቁጥር 17/2019 በቀን 28/12/2018 ዓ.ም ጨረታ ከጥዋቱ በ4፡00

ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የምናካሂድ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ እያሳወቅን፣ የዕቃዎችንና ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ እና ካርጎ ውርስ መጋዘን በመገኘት መመልከት ይቻላል።

10. በሃራጅ ጨረታ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100.00 (አንድ መቶ) APHC CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOM BRANCH OFFICE ስም ይኖርባቸዋል።

11. ለጨረታ የቀረቡት የዕቃዎች ዋጋ ከቫት በፊት የተሰጠ መሆኑ እናሳውቃለን።

12. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች በተናጠል ሳይሆን ለጨረታ ሰነዱ በተሰጠ ኮድ ቁጥር ብቻ የሚሸጥ መሆኑን እናሳውቃለን፣

13. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. በቅ/ጽ/ቤት ደረጃ እየተካሄደ ያለውን የጨረታ አድማስ ለማስፋት ፈጣን የዕቃዎች ማስወገድ ሥራ በማከናወን እና ገቢን በወቅቱ ለመሰብሰብ እንዲቻል ጨረታዎችን በወረቀት አልባ (Online) አሠራር ለማስኬድ ከኦክሽን ኢትዮጵያ ኢማ ጋር ለመሥራት በመታሰቡ ዘወትር ሐሙስ የሚካሄደውን ግልፅ ጨረታ በቀጥታ ሙሉ በሙሉ በኦክሽን ኢትዮጵያ አ.ማ በወረቀት አልባ (Online) የሚካሄድ መሆኑን እናሳውቃለን።

15. የኦክሽን ኢትዮጵያ አ.ማ መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ መስመር +251 905 115 511 በመደወል ማግኘት ይችላሉ

16. በጉምሩክ ኮሚሽን ክፍያ የሚታበ አንድ ጋዜጣ ለቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን እንዲሰጠን እንጠይቃለን፤

ለተጨማሪ መረጃ ቦሌ ኤርፖርት በስልክ ቁጥር 011 668 45 37 እና 011 668 41 93 ደውሎ ይጠይቁ።

በጉምሩክ ኮሚሽን የአ/አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-03
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-09-03 14:15
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Custom Commission Addis Ababa Airport Branch Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 05, 2026)
  • Posted at: 2026-08-05T09:44:22.000Z
← Back to all tenders