External audit and assurance
ሀኪድ በኢትዮጵያ ከ2018 በጀት ዓመት ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የማህበሩን ሂሳብ በውጭ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል
Description
የኦዲት ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
በምዝገባ ሰርተፊኬት ቁጥር 6187 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ተመዝግቦ የሚንቀሳቀሰው ሀገር በቀል ማኅበራችን ሀኪድ በኢትዮጵያ ከ2018 በጀት ዓመት ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት የማህበሩን ሂሳብ በውጭ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡-
- በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የተመዘገበና ሂሳብ ለማድረግ ብቃት ያለው፤
- የምዝገባ እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤
- የወቅቱን ግብር የከፈለ እና
- ተመሳሳይ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ኦዲት ያደረገበትን የሥራ ልምድ ማስረጃ የሚያቀርብ።
ከዚህ በላይ የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉና አስፈላጊውን የሰነድ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ የኦዲት ድርጅቶችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
ስለሆነም መስፈርቱን አሟልተው በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት (5) የሥራ ቀናት የመወዳደሪያ ቴክኒካል ሰነዳቸውን ብቻ (pdf format) ከዚህ በታች በተቀመጠው የኢሜይል አድራሻ መላክ የሚችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።
ኢሜይል፡- [email protected]
ስልክ ቁጥር፦ 09 44 21 10 35 one rea
ሀኪድ በኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ማኅበር
Tender details
- Deadline: 2026-08-11
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት (5) የሥራ ቀናት
- Bid opening: 2026-08-11 17:00
- Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ሀኪድ በኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ማኅበር
- Published on: Addis Zemen (Aug 06, 2026)
- Posted at: 2026-08-06T07:44:28.000Z