Disposal, scrap and surplus sales

በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ አልባሳት፣ ኮንስትራክሽን፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት እቃ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ ጫማዎች፣ ምግብ ነክ፣ ስፔርፓርት፣ የጽዳት እቃ እና ልዩ ልዩ በግልፅ እና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የግልፅ እና የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ

  • የተያዙ የተለያዩ አልባሳት፣
  • ኮንስትራክሽን፣
  • ኤሌክትሮኒክስ፣
  • የቤት እቃ፣
  • የቤት ማስዋቢያ፣
  • ጫማዎች፣
  • ምግብ ነክ፣
  • ለስፔር ፓርት
  • የጽዳት እቃ እና
  • ልዩ ልዩ በግልፅ እና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። 

ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ዕቃዎች ከ05/12/2018 ጀምሮ ሳምል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለጹትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል።

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች ፡-

  1. ለግልፅ እና ለሐራጅ ጨረታ በዘርፍ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤
  2. ለሐራጅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማቅረብ የሚችል፤
  3. ለግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ማቅረብ የሚችል፤
  4. ለሐራጅ ጨረታ ተጫራቹ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል፤
  5. በግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
  6. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን እቃዎች ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት፤
  7. እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሉ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤
  8. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤
  9. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤
  10. ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው እርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፤
  11. ተጫራቹ እቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም፤
  12. ተጫራቾች የሞሉትን የግልጽ ጨረታ ሰነድ ከ05/2/2018 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት የእቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን
  13. ጨረታው በ07/12/2018 3:45 ተዘግቶ ከረፋዱ 4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤
  14. የሐራጅ ጨረታው የሚካሄደው በ07/12/2018 ከረፋዱ 4፡15 በቅ/ጽ/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ መኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤

N.B: አሽናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤

ሳምፕል ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።

በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-13
  • Bid closing time: 10:15
  • Bid closing (note): የሐራጁ መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-08-13 10:15
  • Bid opening (note): የሐራጁ መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
  • Region: Somali
  • Publishing entity: Ethiopian Revenue and Custom Commission Jigjiga Branch Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published on: Addis Zemen (Aug 06, 2026)
  • Posted at: 2026-08-06T08:18:59.000Z
← Back to all tenders