Vehicle and Machinery Sale

በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎች ከ01/12/2018 ጀምሮ በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል።

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች :_

  1. የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፤
  2. ለሐራጅ ጨረታው ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ (C.RO) ማስያዝ የሚችል፤
  3. ተጫራቹ ለሐራጅ ጨረታ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል፤
  4. ተጫራቹ በጨረታ አሸንፎ የገዛውን ተሽከርካሪ ወዲያውኑ ከፍሉ በ05 ቀን ውስጥ የሚረከብ መሆን አለበት፤
  5. ተሽከርካሪ አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤
  6. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤ አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል
  7. ማንኛውም ተጫራች ተሽከርካሪውን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈለግ  እንደቦታው ርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል።
  8. ተጫራቹ ተሽከርካሪውን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፤
  9. የሐራጅ ጨረታው የሚካሄደው በ05/12/2018 ከጠዋቱ 4፡00 በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤

N.B፦

  • አሸናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት) የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ መኪናውን ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ሃላፊነቱን አይወስድም።
  • የቻንሲ እና የሞተር ቁጥር የተመታ ተሽከርካሪ ገዝተው መንገድ ትራንስፖርት ስሌዳ ቁጥር ሲያወጡ መሸጥ እና መለወጥ የማይችሉ እና ቀይ ምልክት ያለው ሰሌዳ በመስጠት በመንገድ ትራንስፖርት በኩል መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

በጉምሩክ ኮሚሽን የጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት

 


Tender details

  • Deadline: 2026-08-11
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-11 10:00
  • Region: Somali
  • Publishing entity: Ethiopian Revenue and Custom Commission Jigjiga Branch Bureau
  • Bid bond: 200,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 06, 2026)
  • Posted at: 2026-08-06T08:22:30.000Z
← Back to all tenders