Stationery

ወላይታ ልማት ማህበር የተለያዩ አይነት የጽ/መሣሪያዎች፣ ላፕቶፕ ኮምፒዩተር፣ ፕላስቲክ ወንበርና ጠረጴዛ፣ ፎቶኮፒ ማሽን እና ሞተር ሣይክል በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

 ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ  ቁጥር ወልማ 03/2026

ወላይታ ልማት ማህበር ለ ‹luminos second chance education project 2026/2027 እ.ኤ.አ ፕሮጀክት ትግበራ የሚውሉ:-

  • በሎት፦ 1- የተለያዩ አይነት የጽ/መሣሪያዎች፤
  • በሎት-2- ላፕቶፕ ኮምፒዩተር፤
  • በሎት- 3-ፕላስቲክ ወንበርና ጠረጴዛ፤
  • በሎት- 4- ፎቶኮፒ ማሽን፣እና
  • በሎት-5-ሞተር ሣይክል፡፡

በግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች አሟልተው መቅረብ ያለባቸው መስፈርቶችና ግዴታዎች

  1. በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፣
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ በሚወዳደሩበት ንግድ ዘርፍ ሕጋዊ ንግድ ስራ ፈቃድ እና ንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሠነድ የማይመለስ ብር 400.00 / አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው የስራ ቀን ድረስ ዘውትር በማህበሩ ሥራ ቀንና ሰዓት በወላይታ ልማት ማህበር አ/አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሰሜን ሆቴል ፊት ለፊት ዳትስን ሰፈር ወደ ግራ በሚያስገባው አስፋልት 100 ሜትር ገባ ብሎ ከሚገኘው ቢሮ እና በወላይታ ሶዶ ወላይታ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት 9 ከሚገኘው ግዥ አስተዳደር ክፍል ቢሮ ቁጥር 13 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ለተሸናፊዎች ከጨረታ ግምገማ በኋላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ለመወዳደር ባቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ በማሰላት 2% በባንክ የተመሠከረለት በወላይታ ልማት ማህበር ስም የተሠራውን ሲፒኦ ከጨረታ ማቅረቢያ ሠነድ ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የውል ማስከበሪያ ዋስትና አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን በኋላ ባሉት ከ5-7 (ሰባት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በአሸነፉበት ዋጋ መጠን ተሰልቶ 10% (አሥር ፐርሰንት) በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሠከረ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡ ለማስያዝ ፈቃደኛ ካልሆነ ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ብር በሙሉ ለማህበሩ ውርስ ይደረጋል፡፡
  6. አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብና አሽናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ አላቀርብም ማለት የጨረታ ዋስትናውን ያስቀጣል፡፡
  7. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውንና የመወዳደሪያ ፓስታቸውን ዋናውንና አንድ ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በ15ኛዉ የስራ ቀንና ሰአት እስከ ዘጠኝ/9፡00/ሰዓት ድረስ በወላይታ ልማት ማህበር ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 13 በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈተው የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በይፋ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 15ኛው የስራ ቀን 9፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነድ በወላይታ ልማት ማህበር ቢሮ ቁጥር 13 ውስጥ በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን ገቢ ሆኖ ልክ በዕለቱ 9፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10፡00 ሰዓት በወላይታ ሶዶ በሚገኘው ወላይታ ልማት ማህበር ግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል ቢሮ ቁጥር 13 ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን በሥራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው ሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓና ቦታ ጨረታው ይከፈታል፡፡
  9. የጨረታ ሠነድ ስርዝ ድልዝ ካለው ወይም ግልጽ ሆኖ ካልታየ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  10. ማሳሰቢያ፡- ልማት ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-0461801191/ 0916833499 መጠቀም ይችላሉ፡፡

ወላይታ ልማት ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-08-24
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በይፋ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 15ኛው የስራ ቀን 9፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-24 15:30
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ በይፋ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 15ኛው የስራ ቀን 9፡30 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Wolaita Development Association
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 07, 2026)
  • Posted at: 2026-08-07T07:12:47.000Z
← Back to all tenders