Disposal, scrap and surplus sales
አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም. ባወጣው ጨረታ ላይ የሽያጭ መነሻ ዋጋው ላይ ስህተት ስላለው ጉዳዩ እስከ ሚስተካከል ድረስ ለባከኑ ቀናት ማካካሻ ይሆን ዘንድ በጨረታ ሰነዱ አንቀፅ 7 መሰረት የጨረታው የጊዜ ገደብ እስከ ነሐሴ 07/2018 ከቀኑ 8፡00 ድረስ የተራዘመ መሆኑን እናሳውቃለን
Description
ለሚመለከተው ሁሉ
ጉዳዩ፡- የጨረታ የጊዜ ገደብ ማራዘምን ይመለከታል፤
ፋብሪካችን የCommon plastic Sheet ምርት ብዛት 1,358,626 ካ.ሜ ሽያጭ ለመፈፀም ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለ10 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ቁጥሩ APF/01/2019/Local የሆነ ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡
ይህን ተከትሎ በጋዜጣው ላይ የታተመው የጨረታ ማስታወቂያ ትክክል ሆኖ እያለ ይህው የጨረታ ማስታወቂያ በመርካቶ ዶት ኮም ድህረ ገፅ ተዘጋጅቶ በፋብሪካችን ዌብሳይት ላይ ሲለቀቅ የሽያጭ መነሻ ዋጋውን ጨምሮ ሌሎች ችግሮች የታዩበት ስለሆነ ጉዳዩ እስከ ሚስተካከል ድረስ ለባከኑ ቀናት ማካካሻ ይሆን ዘንድ በጨረታ ሰነዱ አንቀፅ 7 መሰረት የጨረታው የጊዜ ገደብ እስከ ነሐሴ 07/2018 ከቀኑ 8፡00 ድረስ የተራዘመ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ቀድሞ በስህተት የተገለፀው የምርቱ የአንድ ካሬ ሜትር መነሻ የጨረታ ዋጋ ከነቫቱ ብር 10.40 ነበር።
- አዲሱ የተስተካከለው የምርቱ የአንድ ካሬ ሜትር መነሻ የጨረታ ዋጋ ከነቫቱ ብር 101.40 ነው።
ከዚህ በፊት የወጣውን ጨረታ ለመመልከት ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
https://tender.2merkato.com/tenders/6a6b1b570a538a2f43000001
Tender details
- Deadline: 2026-08-13
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-08-13 14:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara Pipe Factory PLC
- Buyer TIN: 0006196550
- Published on: 2merkato.com (Aug 07, 2026)
- Posted at: 2026-08-07T08:16:01.000Z
- Buyer website: https://amharapipe.et/