Office Machines and Accessories

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን ቋሚ ዕቃ፣ የደንብ ልብስ፣ የጽሕፈት መሣሪያ፣ የጽዳት ዕቃ፣ የህትመት አገልግሎት፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የዲኮር አገልግሎት እና የካፌ መስተንግዶ 1ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን ቋሚ ዕቃ፣ የደንብ ልብስ ፣ የጽሕፈት መሣሪያ፣ የጽዳት ዕቃ የህትመት አገልግሎት፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የዲኮር አገልግሎት እና የካፌ መስተንግዶ 1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች።

1. ለሚጫረቱበት ዕቃዎች ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃና በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ወይም በክልሎች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ መረጃ ማቅረብ የገዙትን ሰነድ ሙሉ መመለስ የምትችሉ።

2. ተጫራቾች ከብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ) ብር በላይ ዋጋ ባለው ግዢ ለመሣተፍ ከፈለጉ ለተጨማሪ እሴት ታክስ /15% ቫት የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርብዎታል።

3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከጠቅላላው ዋጋ 0.5-2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ጽ/ቤት ተብሎ የተዘጋጀ በየሎቱ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ወይም ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት አለባቸው።

4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናል ኮፒ በሚል ተዘጋጅቶ በሰም በታሸገ ኤንቨሎኘ የሚወዳደሩበትን ዋጋ ድርጅታችን ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ሞልተው ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን 10፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 400.00 (አራት መቶ) ብር በመክፈል በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ድርጅታችን ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

6. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 /አሥር/ የስራ ቀናት ፀንቶ ይቆያል ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው አድራሻ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።

7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ለሁሉም ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።

9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን በእያንዳንዱ ዕቃ ዋጋ ላይ ቫት ጨምሮ ያለው ዋጋ እና ከቫት ውጪ ያለውን ዋጋ መግለጽ ይኖርባቸዋል።

10. የቋሚ ዕቃ ናሙና ስታስገቡ በፎቶ ግራፍ የተደገፈ ማቅረብ ይኖርባችኋል።

አድራሻ፡- በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አማኑኤል ቤተክርስቲያን አጂፕ ደጃች አዝማች ኃይሉ ተስፋዬ ት/ቤት ወረድ ብሎ
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-278 1363 መደወል ይችላሉ።
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 3 ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-18
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 /አሥር/ የስራ ቀናት ፀንቶ 10ኛው ቀን 10፡00 ሰዓት ድረስ
  • Bid opening: 2026-08-19 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ketema Sub City Woreda 3 FEDB
  • Buyer address: በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አማኑኤል ቤተክርስቲያን አጂፕ ደጃዝማች ኃይሉ ተስፋዬ ት/ቤት ወረድ ብሎ
  • Bid bond: 0.5-2%
  • Bid document price: 400 (አራት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 07, 2026)
  • Posted at: 2026-08-07T08:16:01.000Z
← Back to all tenders