Office Machines and Accessories

በዶዶላ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የዶዶላ 2ኛ ደረጃ ልዩ አዳሪ ት/ቤት በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎች ለልዩ ልዩ ት/ቤት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 01/2018

በዶዶላ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የዶዶላ 2ኛ ደረጃ ልዩ አዳሪ ት/ቤት በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለፁትን ዕቃዎች ለልዩ ልዩ ት/ቤት አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1. የፅህፈት መሳሪያ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ አላቂና ቋሚ የትምህርት ዕቃዎች፣ የውሃ ቧንቧ ጥገና መሳሪያዎች።

2. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፡

3. የተማሪዎች ዩኒፎርም፣ የሠራተኛ ደንብ ልብስና የስፌት አገልግሎት።

4. የተለያዩ የህትመት አገልግሎት።

5. የተማሪዎች ምግብ አገልግሎት ዕቃዎች፣ ለተማሪዎች ምግብ አቅርቦት የሚሆን ዕህሎችና የዕህል ውጤቶች፣ ፍራፍሬዎችና ለወጣወጥ የሚሆን፣ ቅመማ ቅመማትና ጥራጥሬዎች፣ የማገዶ እንጨት፡

6. የመኪና ዕቃዎች፣ የመኪና ጎማ፣ የመኪና ጥገና።

7. ሞተር ሳይክል፣ ባለሶስት ዕግር ባጃጅ፡

8. የቢሮና የሠራተኞች ሰርቪስ መኪና ኪራይ።

9. የተለያዩ የህንፃዎች ጥገና፣ የኤሌክትሮኒክስና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ጥገና።

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው።

1. ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ዕቃ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለውና ዕቃዎቹን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ VAT ና TIN NO እንዲሁም የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ብቻ።

2. ተጫራቾች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን የሚፈልጉት በምን ዓይነት ዕቃ እንደሆነ በሰነዶቻቸው ላይ በትክክል ለይተው መጻፍ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የዕቃ ስም/Brand Name/ የተመረተበትን ሀገር መግለጽ ይኖርባቸዋል።

4. ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርበትን የዕቃ ዓይነት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ማቅርብ ይኖርበታል። በነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር የነጠላ ዋጋ ይወሰዳል።

5. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ በ15 የስራ ቀናት ውስጥ ቅዳሜ፣ እሁድና የበዓላት ቀን ሳይጨምር በተ.ቁ 1,2,3,4,5,6,7,8 ና 9 የማይመለስ 1000.00 ብር በዶዶላ 2ኛ ደረጃ ልዩ አዳሪ ት/ቤት በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸው ላይ መ/ቤታችን በሰጣቸው የጨረታ ሰነድ ላይ የአንዱ ዋጋ የሚለው ቦታ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላትና የድርጅታቸውን ማህተም በየገፁ፣ ፊርማና ሙሉ አድራሻቸውን በመግለፅ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 3 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ለጨረታ ከቀረቡ ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ፅ/ቤቱ እስከ 20% ለመጨመር ወይም ለመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን በተ.ቁ 1,2,3 ና 4 10,000.00 ብር እንዲሁም በተ.ቁ 5,6,7,8 ና 9 50,000.00 ብር በባንክ የተመሰከረለት (CPO) ወይም ጥሬ ብር በዶዶላ 2ኛ ደረጃ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ማስያዝ አለበት።

9. የሚቀርቡት ዕቃዎች ጥራት ያላቸውና በተሰጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት ተሟልተው መቅረብ ይኖርባችዋል። ተጫራቾች ውል በሚፈርሙበት ጊዜ አጠቃላይ ካሸነፉት ዕቃ ላይ የውል ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን 10% በጽ/ቤቱ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

10. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ ዶዶላ 2ኛ ደረጃ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።

11. በተ.ቁ 1,2,3,4 ና 5 ውስጥ በመ/ቤታችን የተገለፁት ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የሚመለስ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።

12. ጨረታው ከ1/12/2018 ዓ.ም እስከ 22/12/2018 ዓ.ም ድረስ በአየር ላይ ውሎ በ22/12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 3 ውስጥ ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግድም። ዕለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋላ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

13. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 13 40 60 64 / 09 16 42 38 65 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።

የዶዶላ 2ኛ ደረጃ ልዩ አዳሪ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-28
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-28 10:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: DODOLA SPECIAL BOARDING SECONDARY SCHOOL
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 1,000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 07, 2026)
  • Posted at: 2026-08-07T08:40:35.000Z
← Back to all tenders