Office Furniture
በአርሲ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት የጎሎልቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ስር ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፤ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር-ጎወ/1/2019
በአርሲ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት የጎሎልቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ስር ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ኤሌክትሮኒክስ ፈርኒቸር የጽህፈት መሣሪያዎች የጽዳት እቃዎች፤ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም:-
1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑንግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውንያሳደሱ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፉይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) ያላቸው እና በፌዴራል፣ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች እና ለጽህፈት መሣሪያዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 2000 (ሁለት ሺህ) እንዲሁም ለጽዳት እቃዎች ለሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 1500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ) በጽ/ቤቱ ስም በተከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000075143797 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዢና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች በእናት ፖስታ ላይ ሙሉ ስማችሁን ሙሉ አድራሻችሁን የድርጅቱ ማህተም፡ስልክ ቁጥር እና ፊርማ የግድ መሙላት አለባቸው።
5. ተጫራቾች በተራ ቁጥር 1 ላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በአንድ ፖስታ በማሸግ ሁለቱን ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጎሎለልቻ ወረዳ አስተዳደር አዳራሽ ይከፈታል፡፡
6. ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ቃዎች ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች እና ለጽህፈት መሣሪያዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ) እንዲሁም፣ ለጽዳት እቃዎች ለሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15000 (አስራ አምስት ሺህ) በአቅራቢያችሁ በሚገኘው የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ(CPO) ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ አይነት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
8. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ጫንጮ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
9. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር (0910 319 050) (0912 313 241) (0912 289 754) ይጠይቁ።
በአርሲ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት የጎሎልቻ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-26
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-26 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Arsi Zone Gololcha Wereda FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published on: Addis Zemen (Aug 08, 2026)
- Posted at: 2026-08-08T08:23:42.000Z