Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የቢራሮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ለሴክተር ጽ/ቤቶች እና ለቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል እቃዎች በበብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የኮምቦልቻ ሪጆፖሊታን ቢራሮ ክፍለ ከተማ አስ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ የስራ ቡድን በቢራሮ ክፍለ ከተማ ስር ላሉ ለሴክተር ጽ/ቤቶች እና ለቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል

  • ሎት 01 ቋሚ እቃ ፈርኒቸር
  • ሎት ዐ2 የፅህፈት መሳሪያ
  • ሎት ዐ3 የፅዳት እቃ
  • ሎት 04 የደንብ ልብስ የተዘጋጁ ልብሶችና ብትን ጨርቅ
  •  ሎት 05 የደንብ ልብስ ጫማ
  • ሎት 06 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በበብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለሆነም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ / 2019 የወጣውን ጨረታ በማየት ሰነዱን መግዛት የሚችሉ አንገልፃለን፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው

  1. በዘርፉ በዘመኑ የታደለ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርትፍኬት ያላቸው፡፡
  2. የግዥ መጠኑ ክብር 500,000/አምስት መቶ ሽህ ብር / በላይ ከሆነ ተጫራቾች ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፤
  3. በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 2 ላይ የተጠቀሱትና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎሮ ከፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን በጨረታ መክፈቻው ቀን እና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ከተራ ቁጥር 1-2 ላይ የተጠቀሱትን አርጅናል ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ላሉት ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በርPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመስረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ዋጋ 1% ማስያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን የሚያስዙት የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት ብቻ መሆን ይኖርበታል።
  5. ከተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ የጨረታው ዋጋ ፀንቶ ከሚቆይበት የመጨረሻ ተን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 28 ቀናት ፀንቶ ይታያል
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ ብር/ በኮምቦልቻ ቢራሮ ክፍለ ከተማ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 5 በመምጣት በመክፈል ከቀን 30 /2/2019 ዓ.ም እስከ 9/3 2019 ዓ ም ዘውትር በስራ ሰዓት 11፡30 ድረስ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናሉ እና ኮፒውን በተለያየ ፖስጣ በጥንቃቄ በማሸግ በኮምቦልቻ ቢራሮ ክፍለ ከተማ እንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን
  8. ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ከቀኑ 30/2/2019 ዓ.ም / እስከ 9/3/2019 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት 11፡30 ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታው ሳጥኑ በቀን 10/ 3/2019 ዓም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ጨረታው በግልፅ ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጂ የጨረታው መክፈቻ ቀን በዓል ከሆነና የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው የመክፈቻ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. የጨረታው ውድድር የሚካሄደው በጥቅል ድምር ውጤት ስለሆነም የማይሞላ አይተም መኖር የለበትም፡፡ ያልተሞላ ከተገኘ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይደረጋሉ።
  10.  ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ግልፅ ያልሆነ ነገር ሲያጋጥማቸው ጨረታውን ካወጣው አሰሪ መ/ቤት ጋር ከጨረታ መክፍቻ ከ5 አምስት ቀን በፊት በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0912044 564 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  11. የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ ማድረግ ይኖርበታል ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ።
  12. ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተ በኋላ ለ60 ቀን ይሆናል፡፡
  13. ጨረታውን ለማዛባት የሞከሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም በመ/ቤቱ ግዥ የማይሳተፉ እና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወረስ መሆኑን እንገልፃለን፤
  14. ግዥ ፈዋሚው አካል ከአሽናፊ ተጫራች ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት በአሸናፊውተጫራች በውድድር የተገኘ ዋጋ ሳይቀየር በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው የአቅርቦት መጠን ላይ እስክ 20% /ሃያ በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ የሚቻል ይሆናል፡
  15. ለሎት ዐ4 እና ለሎት 05 በክ/ከተማው ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 5 በተቀመጠው ሳፕል/ናሙና መሰረት በማየት ሰነዱን መሙላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  16.  የጨረታ አሸናፊው ድርጅት ንብረቱን በምቦልቻ ቢራሮ ክ/ከተማ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  17. ክ/ተማው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የቢራሮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-11-19
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-11-19 10:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: የቢራሮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት
  • Bid bond: 1% ለእያንዳንዳቸው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Nov 09, 2026)
  • Posted at: 2026-11-09T10:32:25.000Z
  • Source: Qelal Tenders
← Back to all tenders