Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳዳር የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ለ2019 በጀት አመት የተለያዩ የጽዳት እና የቢሮ የጽህፈት መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ድ/ዳ/አ/ኢ/ኢ/ቢ/0002/2019
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳዳር የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ለ2019 በጀት አመት የተለያዩ የጽዳት እና የቢሮ የጽህፈት መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ነጋዴዎች እንዲሳተፋ ይጋብዛል፡፡
1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር ከፍሎ የ2019 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፣
2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፣
3. የቫት ተመዝጋቢ ሆኖ የምዝገባ ሰርተፊኬት አያይዞ ማቅረብ የሚችል፤
4. በአቅራቢነት ዝርዝር ላይ የተመዘገበ ሆኖ የምስክር ወረቀት ያለው፣
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ለፅዳት እቃዎች ብር 5,000.00/አምስት ሺህ/ ና ለፅፈት መሳሪያ ብር 7000( ሰባት ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ፤በጥር ገንዘብ ከመወዳደሪያ ዋጋቸው ጋር አያይዘውና አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
6. ተጫራቶች የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል ሰነዱን በመግዛት እና የመጫረቻ ዋጋቸውን በመሙላል ይህ ጨረታ በድሬ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በድሬዳዋ አስተዳዳር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ግዥ ክፍል ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
7. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ተጫራቶች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት 4፡00 ላይ ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻው በእረፍት ቀን ላይ ከዋለ በቀጣዩ ስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፣
8. ተጫራቶች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተገለጸላቸውና ውል ከፈጸሙ በኃላ ወዲያውኑ በ10 ቀናት ዉስጥ ያሸነፉባቸዉን እቃዎች በሙሉ በራሳቸው ትራንስፖርት ለቢሮአችን ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ አለባቸዉ
9. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፤፤
ለተጨማሪ መረጃ 0920 459 974 / 0915 763 171 ይደውሉ
የድሬዳዋ አስተዳዳር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-11-19
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ በድሬ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-11-19 10:00
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ በድሬ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Dire Dawa
- Publishing entity: Dire Dawa Administration Trade, Industry and Investment Bureau
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Melekite Dire (Nov 04, 2026)
- Posted at: 2026-11-09T10:25:29.000Z
- Source: Qelal Tenders