Building and Finishing Materials

በደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የጂንካ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚውል የተለያዩ የግንባታ ማቴርያሎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የሳይት እና የቢሮ ሰርቪስ መኪናዎች የሻወር ትራክ ቦቴን ጨምሮ፣ ጽህፈት መሳሪያ፣ የንጽህና መጠበቂያ እና የተለያዩ የተሽከርካሪ እና ማሽን መለዋወጫ የመጀመሪያ ዙር በወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የመጀመሪያ ዙር የመጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የጂንካ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚውል የተለያዩ የግንባታ ማቴርያሎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የሳይት እና የቢሮ ሰርቪስ መኪናዎች የሻወር ትራክ ቦቴን ጨምሮ፣ ጽህፈት መሳሪያ፣ የንጽህና መጠበቂያ እና የተለያዩ የተሽከርካሪ እና ማሽን መለዋወጫ የመጀመሪያ ዙር በወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማስገባት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው መስፈርት

1. በጨረታው ለመሳተፍ በመስኩ የንግድ ፍቃድ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ ቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ፣ የምስክር ወረቀት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. ዋጋ የሚያቀርቡበትን የጨረታ ሰነድ ፋይናንሻሉን አንድ እና ኦርጅናል አንድ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ በማድረግ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና አድራሻቸውን በትክክል ማስፈር ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን የንጽህና እቃዎች እና የግንባታ እቃዎች ሳምፕል ማለትም ለብረት 50ሣ ቁርጥራጭ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

4. ተጫራቾች አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች በራስ ትራንስፖርት ጂንካ ዲስትሪክት ጊቢ መጋዝን ድረስ በማጓጓዝ የሚያስረክቡ ይሆናል።

5. ተጫራቾች ከዚህ ቀደም መ/ቤቱ ባወጣቸው የአገልግሎት ሆነ የእቃ ግዥ ጨረታዎች የጨረታ ሂደት ላይ እና ከጨረታ በኋላ ያሸነፉትን ያላስገቡ ሆን ብለው የመንግስትን ስራ ያላስተጓጎሉ እና ከማንኛውም አይነት የዲስፕሊን ክስ እና ቅጣት ነጻ የሆኑ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

6. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክር ተጫራች ከጨረታው የሚሰረዝ ሆኖ ለወደፊቱም መ/ቤቱ በሚያወጣቸው የአገልግሎት እና እቃ የግዥ ጨረታዎች ላይ እንዳይሳተፍ ይደረጋል።

7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ጂንካ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ፋይናንስና ሎጂስቲክስ ቢሮ ቁጥር 01 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን በነጻ መውሰድ ይችላሉ።

8. የጨረታ ጊዜው በአዲስ ዘመን ጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ (15) አስራ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ፀንቶ ይቆያል።

9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ(15) አስራ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ይቆይና በማሸግያው አስራ ስድስተኛው የስራ ቀን ከቀኑ 9፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሣጥኑ ይታሸግና በ9፡30 ይከፈታል።

10. ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ30 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።

11. ተጫራቾች ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ለእቃ ግዥ 5000 አምስት ሺህ ብር/ ለአገልግሎት ግዥ ማለትም ለተሽከርካሪ ኪራይ 10,000 /አስር ሺህ ብር በካሽ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ/CPO/ ከሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. በጨረታው የቀረቡ የአገልግሎት ግዥ ሆነ የእቃ ቁጥሩን እንደአስፈላጊነቱ መ/ቤቱ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።

ለበለጠ መረጃ 0916853591 / 0930755002
በደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የጂንካ ዲስትሪክት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-27
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን ከቀኑ 9፡00
  • Bid opening: 2026-08-27 15:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን ከቀኑ 9፡30
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: South Ethiopia Roads Authority
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published on: Addis Zemen (Aug 09, 2026)
  • Posted at: 2026-08-10T07:47:00.000Z
← Back to all tenders