Audio-visual, photography and graphic design
የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን በዋናው መስሪያ ቤት ግቢ ውስጥ እና በቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ያሉትን የአይረን ኦር (iron ore) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ ማሰታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ቁጥር-EMC/OT/NCB/02/2019
የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን በዋናው መስሪያ ቤት ግቢ ውስጥ እና በቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ያሉትን የአይረን ኦር (iron ore) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
|
ሎት |
የዕቃው ዓይነት |
ብዛት |
የመጫረቻ ሰነድ የሚቀርብበትና የሚዘጋበት የመጨረሻ |
የመጫረቻ ሰነድ የሚከፈትበት |
||
|
ቀን |
ሰዓት |
ቀን |
ሰዓት |
|||
|
1 |
የአይረን ኦር ( iron ore)72ቶን ውስጥ ግምታዊ 0.087 % ሊደርስ የሚችል የታንታለም አዘል መአድን ሊኖረው ይችላል |
81.9 ton |
21/12/2018
|
4:00
|
21/12/2018
|
4:30
|
በዚሁ መሰረት ተጫራቾች ለመወዳደር ሲመጡ ማሟላት የሚገባቸው ግዴታዎች፡-
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የግዥ ዓይነት በዘርፉ ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (Value added tax) ተመዝጋቢ መሆናቸውን፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN)፣ እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችላቸው ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሚሰጥ የታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። እንዲሁም የማዕድን ማዘዋወርና ማስተላለፍ ፈቃድ ያለው መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በዚህ ማስታወቂያ በስተመጨረሻ በተገለጸው አድራሻ በቢሮ ቁጥር ብሎክ 2 በግንባር በመቅረብ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 / ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ሶፍት ኮፒ( soft copy ) መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ግዥ የሚፈጽሙበትን 2% (2 በመቶ) በኢትዮጵያ ማአድን ኮርፖራሽን ስም(Ethiopian Mineral Corporation) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው አሸናፊዎች ከታወቀ በሶስተኛው ቀን በማስታወቂያ ቦርድ ይለጠፋል።
- የጨረታ አሸናፊዎች ባስገቡት ዝርዝር መሰረት ገንዘቡን ከከፈሉበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀን ውስጥ ንብረቱን ማንሳት አለባቸው። የጭነት ማጓጓዟ የማቅረብ ሃላፊነት የገዥ ይሆናል። ሎት 1 ላይ ያለውIRON ORE 72 Tone( በውስጡ ግምታዊ 0.087 % ሊደርስ የሚችል የታንታለም አዘል መአድን ሊኖረው ይችላል ) የሚገኘው ቀንጢቻ ከ አ.አ 550 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሲሆን ቀሪው 9.9 ቶን አይረን ኦር ዋናው መስሪያ ቤት አ.አ ይገኛል ፤ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
- ተጫራቾች በመጫረቻ ሠነዳቸው ላይ ሶስት ማህተም ያረፈበት በማድረግ በፖስታው ጀርባ ላይ የድርጅታቸውን ስም፤የጨረታውን ሎትና ዓይነት፤ሙሉ አድራሻቸውን ጽፈው እና ፈርመው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው እና የሚከፈተው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለጸው ቀን መሰረት ሲሆን የመዝጊያ እና መክፈቻ ቀኑ በበዓል ቀን ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች በሚሰጡት የዕቃ ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT)የማካተት ግዴታ አለባቸው ነገር ግን ተጫራቹ የተጨማሪ እሴት ታክስን ካላካተቱ ኮርፖራሽኑ ተጫራቹ በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ቫትን ጨምሮ ይወሰዳል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- 22 ማዞሪያ አውራሪስ ሆቴል አጠገብ
በስልክቁጥር 0911622263 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-08-27
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-08-27 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Mineral Corporation (EMC)
- Buyer address: 22 ማዞሪያ አውራሪስ ሆቴል አጠገብ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Aug 09, 2026)
- Posted at: 2026-08-10T09:06:11.000Z