Audio-visual, photography and graphic design
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 1147/11፣ 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪ ስም |
የንብረት አስያዥ |
የማሽነሪው አገልግሎት |
ማሽነሪው አይነት |
ኢንቮይስ ቁጥር |
ግምት
|
ሓራጁ የሚከናወንበት ቀን እና ሰዓት |
|
1 |
ኤፍራታ ኃ/የተ/የግ/ማ |
ተበዳሪው
|
ሞተር መገጣጠም |
Motor cycle assembly line |
SQ20150822
|
27,793,788.064
|
18/12/2018 ዓ.ም 3፡00-4፡00 ጠዋት |
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
የመያዝ ንብረቱ መለያ |
የሐራጅ መነሻ ዋጋ (ብር)
|
ሐራጁ የሚከናወንበት ቀን እና ሰዓት |
|||
|
አድራሻ |
የይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር መለያ |
የይዞታው ስፋት (በካ.ሜ) |
የይዞታው አይነት የሚሰጡ አገልግሎት |
|||||
|
2 |
ሸሙ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
ተበዳሪው |
ድሬ ዳዋ ከተማ፣ ቀበሌ 02 |
2791 እና መ/ል/ሊ/3124 |
12,224
|
ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውሉ ግንባታዎች ያረፉበት ይዞታ፣ የምግብ ዘይት አና የሳሙና ማምረቻ ማሽነሪዎች |
1,020,580,515
|
03/13/18 ዓ.ም 3፡00-4፡00/ጠዋት
|
|
3 |
ሽሙ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
|
ተበዳሪው |
ድሬ ዳዋ ከተማ፣ ቀበሌ 02 |
መ/ል/ሊ 1279
|
10,000
|
ለኢንዱስትሪ |
72,975,829.16
|
03/13/18 ዓ.ም 4፡00-5፡00 ጠዋት |
|
4 |
አቶ ማሙሽ ተስፋዬ ዱብሬ
|
ተበዳሪው |
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን ዞን ቅምብቢት ወረዳ ሸኖ ከተማ ቀበሌ 01 |
138/10 |
400 |
መኖሪያ ቤት |
2,255,821.84 |
03/13/18 ዓ.ም 5:00-6:00 ጠዋት |
|
5 |
ሪሳ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር |
አቶ አትናቲዎስ ገ/እግዝአብሔር |
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሽዋ ዞን ሰንዳፋ ከተማ |
640/PDR/302/99 |
21,600
|
የንግድ ሕንፃ
|
35,955,053.37
|
03/13/18 ዓ.ም 7:00-8:00 ከሰዓት |
|
6 |
አቶ ለገሰ ሙለታ ያሚ እና የሰውዘር አለበል ኃይሉ |
ተበዳሪዎች
|
ሻሸመኔ ከተማ አለቼ ክ/ከተማ አዋሾ ወረዳ 01 ቀበሌ |
WBIFBG/A/L/937/09 |
5000 |
ለፋብሪካ አገልግሎት የሚውል ሕንጻ |
38,071,965.73
|
03/13/18 ዓ.ም 8:00-09:00 ከሰዓት |
|
7 |
አቶ ከተማ ነገሱ ጉተማ |
ተበዳሪው
|
በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 03 |
ለ/ኩ/9/7/6/158308/00
|
54.85 |
ንግድ ቤት |
2,719,062 21 |
03/13/18 ዓ.ም 9፡00_10፡00 ጠዋት |
|
8 |
ባኑ ሃበሻ ቢዝነስ ግሩፕ ኃ/የተ/የግ/ማ |
አቶ ሽፈራው ሞገስ |
በአዲስ አበባ ከተማ፣ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ክ፤ ወረዳ 07 |
AA000070704660 |
210 |
ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል ይዞታ
|
7,743,775,99
|
04/13/18 ዓ.ም 3፡00-4፡00 ጠዋት |
|
9 |
ባኑ ሃበሻ ቢዝነስ ግሩፕ ኃ/የተ/የግ/ማ |
ወ.ሮ ዘነበች ተደላ
|
በኦሮሚያ ክልል ካሸገር ሲቲ ዩኒሳ አካባቢ |
029962/1
|
338 |
ለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚውል ይዞታ |
32,699,958.88
|
04/13/18 ዓ.ም 5፡00-6፡00 ጠዋት |
|
10 |
አቶ ሱራፌል ወርቅነህ |
አቶ ሃ/ማርያም ወልደየስ ወይ.እመቤት በዛብህ |
በአዲስ አበባ ከተማ፣ ቦሌ ክ/ክ፤ ወረዳ 01 ቦሌ አየር መንገድ ካርጎ መግቢያ |
AA000060103191
|
700 |
ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውል G+3+T |
50,509,681.04 |
04/13/18 ዓ.ም 5፡00-6፡00 ጠዋት |
|
11 |
ዋጋዬ ካሳዬ ሙላት |
ወ/ሮ አቦነች አሰፋ |
አርባ ምንጭ ከተማ ሴቻ ክፍለ ከተማ ሼቻ ቀበሌ |
በቀድሞ አ/ከ/አ 366፤ በአዲሱ SD_10 |
400 |
መኖሪያ ቤት |
12,929,784.02
|
04/13/18 ዓ.ም 8:00-9:00 ከሰዓት |
|
12 |
አቶ ደግነህ ገ/ስላሴ መገኑ |
ተበዳሪው
|
የመኖሪያ ቤት
|
AA000060704272 |
287.00 |
በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 |
13,498,167.56
|
04/13/18 ዓ.ም. 9:00-10:00 ከሰዓት |
|
13 |
አቶ ዳዊት ታደሰ ሞላ |
እነ መክብብ ደምሴ ሽበሽ |
በኮምቦልቻ ከተማ፤ ቀበሌ 04 |
3457/ሊዝ//ኮ/ቴ/አገ/ቀ04/2002 |
2500 |
መኖሪያ ህንፃ |
9,480,116.30
|
03/13/18 ዓ.ም 3፡00-4፡00 ጠዋት |
|
14 |
አቶ ኃይለማሪያም ክንዴ |
ተበዳሪው
|
በደብረ ማርቆስ ከተማ፣ተድላ ጓሉ ክ/ከተማ፣ ቀበሌ 12 |
K/2004
|
200.00 |
መኖሪያ ቤት |
2,389,326.28
|
03/13/18 ዓ.ም 4:00-5:00 ጠዋት
|
በመሆኑም፡-
1. ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) በማስያዝ መጫረት ይችላል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲፒኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው።
2. ከተ.ቁ 1-12 የተዘረዘሩ ንብረቶች ጨረታ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋናው መስሪያ ቤት 42ኛ (ወለል) ፎቅ ቢሮ ቁጥር 4203 ነው፤ በተራ ቁጥር 13 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ጨረታ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደሴ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ዉስጥ፣ በተራ ቁጥር 14 ላይ የተጠቀሰው ንብረት ጨረታ የሚከናወነው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደብረ ማርቆስ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ዉስጥ ነው።
3. የንግድ ማህበርን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ እና መተዳደሪያ ደንብ የያዘና በማህበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል።
4. ከመኖሪያ ቤቶች በስተቀር ለጨረታ የቀረቡ ንብረቶችን በጨረታ አሸንፎ የገዛ በሽያጩ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል።
5. የጨረታ አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።
6. ንብረቶቹን ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት 42 ፎቅ በአካል በመቅረብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም መሰረት መጎብኘት ይቻላል።
7. በጨረታው ከፍተኛ የሆነ የጨረታ ዋጋ የሰጠ ተጫራች በባንኩ የጨረታ አሸናፊነት ደብዳቤ ከደረሰው ቀን ጀምሮ ቀሪ የሽያጩን ገንዘብ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጁ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
8. ንብረቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም። ገዢው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል።
9. ባንኩ ሐራጁን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111-13-05-08 በመደወል ወይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲሱ ዋና መ/ቤት 42ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ሕግ ክፍል በአካል ቀርቦ ማነጋገር ይቻላል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
Tender details
- Deadline: 2026-09-09
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): የጨረታው ቀን እና ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-09-09 16:00
- Bid opening (note): የጨረታው ቀን እና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Commercial Bank of Ethiopia
- Bid bond: 25%
- Published on: Reporter (Aug 09, 2026)
- Posted at: 2026-08-10T11:18:48.000Z
- Buyer website: https://www.combanketh.com