Building Construction

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ አውሮፕላን ማረፊያ የተርሚናል እድሳትና ማስፋፊያ፣ የአውሮፕላን መንደርደሪያ እና ተጨማሪ መገልገያዎች ንድፍና ግንባታ ፕሮጀክት (Design And Build of Asosa Airport Terminal Renovation and expansion, Runway Strip and Ancillary Facilities Construction Project) ብቁ የ

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: - SSNT-T634

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ አውሮፕላን ማረፊያ የተርሚናል እድሳትና ማስፋፊያ፣ የአውሮፕላን መንደርደሪያ እና ተጨማሪ መገልገያዎች ንድፍና ግንባታ ፕሮጀክት (Design And Build of Asosa Airport Terminal Renovation and expansion, Runway Strip and Ancillary Facilities Construction Project) ብቁ የህንጻ ተቋራጭ ተወዳዳሪዎችን ለመጋበዝ ይፈልጋል።

የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ በ365 የቀን መቁጠሪያ ቀናት ውስጥ ይሆናል፣ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች፣ አስፈላጊውን የሰው ሃይል፣ ማሽንና የግንባታ ግብዓት ማሟላት የሚችሉ ሥራ ተቋራጮች ሥራውን ለማከናወን ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡

1. በዘርፉ ለመሥራት ለ2018 ዓ.ም /2025/2026 እ.ኤ.አ. ከንግድ ሚኒስቴር የተሰጠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣

2. በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በሁለት (2) እና ከዚያ በላይ ፕሮጀክቶች ላይ የተሰማሩ ተጫራቾች የእያንዳንዱ ፕሮጀክት አፈፃፀም ከ70% በታች ከሆነ በዚህ ጨረታ መሳተፍ አይችሉም፡፡

3. በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል ለ2018 ዓ.ም ለ2025/2026 G.C/ የታደሰ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ (GC/BC-1 የሆነ፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣

4 የሀገር ውስጥ ተጫራቾች የተሰማሩበትን የሥራ ዘርፍ የሚያሳይ ሕጋዊ የሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ እና በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን የአቅራቢዎችና አገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆን ይገባቸዋል፣

5. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ::

6. የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ከታክስ እዳ ነጻ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል::

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (100.00 ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T634 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ፡፡

8. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት አምስት መቶ ሺህ ብር (500,000.00 ብር) ተመጣጣኝ የውጭ ሀገር ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለባቸው። ከማንኛውም ኢንሹራንስ እና ውስንነት ያለው የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡

9. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለአንድ መቶ ሃምሳ (150) የቀን መቁጠሪያ ቀናት የጸና ይሆናል፡፡

10. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ከፍል ጳጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ

ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ

ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል

ወ/ሮ ሰላማዊ አባተ

ስልክ ቁጥር 011-517- 4258

ኢ-ሜይል: Email: [email protected]

አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-07
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid opening: 2026-09-07 15:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Airlines Group (ETG)
  • Buyer TIN: 0000028498
  • Bid bond: 500,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 09, 2026)
  • Posted at: 2026-08-10T12:20:12.000Z
← Back to all tenders