Materials
በጉለሌ ክ/ከተማ የመድኃኔዓለም አጠ/2ኛ ደረ/ት/ቤት ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ የተለያዩ ዕቃዎችን ግዢ መፈጸም ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- መድ/አጠ 2ኛ/ደረ/ት/ቤት 02/2019 ዓ/ም
በጉለሌ ክ/ከተማ የመድኃኔዓለም አጠ/2ኛ ደረ/ት/ቤት ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ የሚከተሉትን ዕቃዎች ግዢ መፈጸም ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡-
- ሎት 1 ለጽህፈት እና ለትምህርት መሳሪያዎች 34,144.26ብር /ሰላሳ አራት ሺህ አንድ መቶ አርባ አራት ብር ከሀያ ስድስት ሳንቲም/
- ሎት 2 ለጽዳት ዕቃዎች 20,000 ብር /ሀያ ሺህ ብር/
- ሎት 3 ለደንብ ልብስ ዕቃዎች 62,400 /ስልሳ ሁለት ሺህ አራት መቶ ብር/
- ሎት 4 ለአላቂ የህክምና ዕቃዎች 400ብር /አራት መቶ ብር/
- ሎት 5 ለኤሌክትሪክ እና ለህንጻ እቃዎች 12,955.74ብር /አስራ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሀምሳ አምስት ብር ከሰባ አራት ሳንቲም/
- ሎት 6 ለስፖርት ዕቃዎች 1,000 ብር /አንድ ሺህ ብር/
- ሎት 7 ለደንብ ልብስ ስፌት 1,000 ብር /አንድ ሺህ ብር/
- ሎት 8 ለቋሚ ዕቃዎች 10,000 ብር /አስር ሺህ ብር/
- ሎት 9 ለጭነት እና ጉልበት አገልግሎት 10,000 ብር /አስር ሺህ ብር/
- ሎት 10 የትምህርት ቤቱን ከበብ ለማከራየት 55,123.20/ሀምሳ አምስት ሺህ አንድ መቶ ሀያ ሶስት ብር ከሀያ ሳንቲም/
- ሎት 11 የግቢ ውስጥ ጥገናዎች 21,000ብር /ሀያ አንድ ሺህ ብር/
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ በማስያዝ መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፣
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር የከፈለ
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር በአቅራቢነት የተመዘገቡና የምዝገባ ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
3. ተጨማሪ የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
4. የግብር ከፋይነት ምዝገባ ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
5. በሁለትና ከዛ በላይ ሎት ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ለእያንዳንዱ ሎት የተሟላ ማስረጃ በማያያዝ በተለያዬ ፖስታ በማሸግ መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን የተሟላ ማስረጃ የሌለው ሎት ውድቅ ይሆናል።
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
7. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን ከት/ቤቱ ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 17 በሎት የማይመለስ ብር 200 በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ።
8. በመንግስት የተደራጁ ልዩ አስተያዬት የሚደረግላቸው ድርጅቶች በድጋፍ ደብዳቤ መሳተፍ የሚችሉት እራሳቸዉ ባመረቱት እቃዎች ላይ ብቻ ነው።
9. ት/ቤቱ ከሚገዛው ዕቃ ግዢ ላይ ከውል በፊት 20% መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል።
10. አሸናፊው ድርጅት ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ አለበት።
11. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ እስከ ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማድረስ አለበት።
12. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ በወሰዱት ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ ዋጋውን በመሙላት የግዢውን አይነትና የድርጅቱን ሙሉ ማስረጃ የታሸገው ፖስታ ላይ በመጻፍ ኦርጅናልና ኮፒ ፖስታ ላይ የድርጅት ማህተብና ፊርማ በማስቀመጥ ለዚሁ ተብሎ የተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
13. ለሚያቀርቡት ዕቃዎች ፖስታውን ስያስገቡ ናሙና ለሚያስፈልጋቸውን ዕቃዎች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ናሙናዎች መግባት አለባቸው።
14. ትምህርት ቤቱ ካስቀመጠው ተፈላጊነት /specification/ አንሰው ወይም በልጠው የሚመጡ ናሙናዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
15. ጨረታው በ 10ኛው ቀን 10፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት የከፈታል።
16. ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት ያሸነፈውን ጠቅላላ የዕቃዉን መጠን 25% እስከ 6 ወር ድረስ ተጨማሪ ቢጠየቅ በራሱ ዋጋ የሚያቀርብ ይሆናል።
17. ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
የመድኃኔዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አለፍ ብሎ ቶታል ፊት ለፊት ይገኛል።
ስልክ: 0112 593 437 / 0112 593 438
በጉለሌ ክ/ከተማ የመድኃኔዓለም አጠ/2ኛ ደረ/ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-30
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ቆይቶ በ10ኛው ቀን 10፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-01 10:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: የመድኃኔዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር በሎት
- Published on: Addis Zemen (Sep 19, 2026)
- Posted at: 2026-09-19T08:11:13.000Z
- Source: 2merkato