Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቃ/ቃሊቲ ክ/ከተማ የህብረት ችቦ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የ2019 በጀት ዓመት የስፖርት መምህራን ትጥቆች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የሕትመት ሥራዎች፣ አላቂ የሕክምና ዕቃዎች፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣ ሌሎች የፅዳት ዕቃዎች፣ ልዩ ልዩ መሣሪያዎችና መጻሕፍት፣ ቋሚ ዕቃዎች አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019 በ2019 በጀት አመት 1ኛ ዙር
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቃ/ቃሊቲ ክ/ከተማ የህብረት ችቦ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የ2019 በጀት ዓመት የስፖርት መምህራን ትጥቆች፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የሕትመት ሥራዎች፣ አላቂ የሕክምና ዕቃዎች፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣ ሌሎች የፅዳት ዕቃዎች፣ ልዩ ልዩ መሣሪያዎችና መጻሕፍት፣ ቋሚ ዕቃዎች አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
ጨረታው ከመከፍቱ በፊት በቀረበው የተጫራቾች ለሚወዳዳሩበት ዕቃ የጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የገዙትን ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ብለው በመፃፍ ለየብቻ በማዘጋጀት ፊርማና ማህተም በማሳረፍ ጨረታው ለእያንደዱ ሎት የምታቀርቡት የሲ.ፒ.ኦ መጠን 6211=36,000 (ሰላሳ ስድስት ሺህ ብር) 6212=23,480 (ሃያ ሶስት ሺህ አራት መቶ ሰማንያ ብር) 6213=443 (አራት መቶ አርባ ሶስት ብር) 6214–200 (ሁለት መቶ ብር) 6215=28,000 (ሃያ ስምንት ሺህ ብር) 6218= 22,000 (ሃያ ሁለት ሺህ ብር) 6219=2,400( ሁለት ሺህ አራት መቶ ብር) 6313= 19,500 (አስራ ዘጠኝ ሺህ አምስት መቶ ብር) የምታቀርቡ ሲሆን የጨረታ መስፈረት ከዚህ በታች እንደሚመለከተው ይሆናል
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድና ምዝገባ ፍቃድ ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢና የዘመኑ የታደሰ ግብር ከፋይ መለያ ያላቸው
- የአቅራቢትን ምዝገባ ምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ
ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፍል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የህብረት ችቦ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንሰ ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይቻላል። የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋት 2፡30 እስከ 11፡00 ፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይቻላል። ጨረታው በ11ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሳጥን ተዘግቶ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ የህብረት ችቦ የመ/ደ/ት/ቤት ይከፈታል።
የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ያለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም። የጨረታው አሸናፊዎች ከታወቀ በኋላ ለተሸናፊዎቹ ያስያዙት ገንዘብ ወዲያው ይመለስላቸዋል። ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።እንዲሁም ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታው አሸናፊዎቹም ተለይተው በተገለፀው በተከታታይ 5 የሥራ ቀናት ውስጥ አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መፈፀም አለባቸው። ተሸናፊዎቹ ደግሞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያው ይመለስላቸዋል። አሸናፊዎች በገቡት ውል መሰረት ዕቃዎችን ተቋሙ ድረስ የማቅረብ ግዴታ አላባቸው። መሥሪያ ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራቶች አምራች መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማምጣት አለባቸው። በድጋፍ ደብዳቤ የማናስተናግድ መሆኑ እናሳውቃለን።
አድራሻ፡- አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 ልዩ ስሙ ሳሪስ አቦ አዋሽ ቆዳ አጠገብ የህብረት ችቦ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
ስልክ ቁጥር 011 443 1698
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቃ/ቃሊቲ ክ/ከተማ
የህብረት ችቦ ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-10-01
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የሥራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-01 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የሥራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Akaki kality Sub City Wereda 6 Hebert Chibo Elementary School
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 19, 2026)
- Posted at: 2026-09-19T08:48:06.000Z
- Source: 2merkato