Sport Materials and Equipment
ናታኒም የበጎ አድራጎት ድርጅት በ“CADiR” (Collective Action for Disability Rights) ፕሮጀክት አማካኝነት ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችና ወጣቶች አገልግሎት የሚውሉ የድጋፍ ሰጪ፣ የስፖርት፣ የቴራፒ እና የተሃድሶ ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ Ref No: NCO/0456/2026
የድጋፍ ሰጪ፣ የስፖርት እና የቴራፒ ቁሳቁሶች ግዢ
ናታኒም የበጎ አድራጎት ድርጅት በ“CADiR” (Collective Action for Disability Rights) ፕሮጀክት አማካኝነት ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችና ወጣቶች አገልግሎት የሚውሉ የድጋፍ ሰጪ፣ የስፖርት፣ የቴራፒ እና የተሃድሶ ቁሳቁሶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1. ስለ ናታኒም በጎ አድራጎት ድርጅት (Natanim Charitable Organization - NCO)
ናታኒም የበጎ አድራጎት ድርጅት (NCO) በሚያዚያ 5 ቀን 2015 ዓ.ም. (License No. 6792) የተመዘገበ ሀገር በቀል ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን፣ በአእምሮ ጤና፣ በማህበራዊ ድጋፍ (psychosocial support) እና አካል ጉዳተኞችን በማካተት ላይ ትኩረት አድርጎ ይሰራል። NCO ከመንግስት ተቋማት፣ ከትምህርትና ጤና ዘርፎች፣ ከሌሎች በጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ከአካል ጉዳተኞች ማህበራት (OPDs) ጋር በትብብር ይሰራል።
2. የሚፈለጉ የመሣሪያዎች እና ቁሳቁሶች ምድብ (Procurement Categories / Lots)
- Lot A: Assistive & Adaptive Sports Equipment (የድጋፍ ሰጪ ስፖርት ቁሳቁሶች)
- Lot B: Sensory, Therapy & Rehabilitation Equipment (የቴራፒና የተሃድሶ ቁሳቁሶች)
3. የጨረታው ተሳታፊዎች ማሟላት የሚገባቸው ዋና ዋና መስፈርቶች
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ: በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የቫት (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑበት ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- የብራንድና ቴክኒክ መግለጫ (Brand & Specifications): ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው እቃዎች በሙሉ ብራንድ (Brand)፣ የአምራች ስም (Manufacturer) እና ዝርዝር የቴክኒክ መግለጫ (Market Specific Specification) በግልጽ ማመልከት አለባቸው።
- የትራንስፖርትና ማጓጓዣ አገልግሎት (Transport Service Declaration): አቅራቢዎች ዕቃዎቹን እስከ ናታኒም በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ጽ/ቤት (አዲስ አበባ) ድረስ የማጓጓዝ አገልግሎት የሚሰጡ መሆኑን ወይም የማይሰጡ መሆኑን በፋይናንሻል ፕሮፖዛላቸው ላይ በግልጽ መጥቀስ አለባቸው።
- የዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት (Mandatory Price Quotation Format): ተጫራቾች በተሰጠው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርማት (Quantity Offered = 1) መሠረት የአንድ ዕቃ አጠቃላይ የገበያ ዋጋ ተመን (Price of One Unit) ማቅረብ አለባቸው።
- የማስረከቢያ ጊዜና ዋስትና: የአቅርቦት ጊዜ ሰሌዳ እና ለኤሌክትሮኒክስ/ሜካኒካል ዕቃዎች የዋስትና (Warranty) ጊዜ ማቅረብ አለባቸው።
4. የጨረታ ማስገቢያና መክፈቻ ጊዜ ሰሌዳ
- የጨረታው ማስታወቂያ የሚወጣበት ቀን: ቅዳሜ፣ መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም. / September 19, 2026
- የጨረታ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን፡ ቅዳሜ ፣ መስከረም 23 ቀን 2018 ዓ.ም. / Friday, October 03, 2026 ከቀኑ 11:00 ሰዓት በፊት።
- የጨረታ መክፈቻ ቀን፡ ማክሰኞ፣ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም. / Tuesday, October 06, 2026 ከቀኑ 2:30 ሰዓት ላይ።
አቅራቢዎች የጨረታ ሰነዱን (ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ፕሮፖዛልን) በሁለት የተለያዩ ኢንቭሎፖች ታሽገው በተፈረሙ ፖስታዎች በማድረግ፣ በአጠቃላይ በሶስተኛ ጥቅል ፖስታ ውስጥ በማሸግ በናታኒም በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ጽ/ቤት አዲስ አበባ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 02 በአድራሻችን በአካል በመገኘት ማስገባት ይችላሉ።
ማሳሰቢያ: ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡
ናታኒም የበጎ አድራጎት ድርጅት
ስልክ፡ 0993252797 / 0945482424
ኢሜይል: [email protected] , [email protected]
አድራሻ፡ አዲስ አበባ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 02
Tender details
- Deadline: 2026-10-03
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-10-06 08:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Natanim Charitable Organization (NCO)
- Buyer TIN: 0084298990
- Published on: 2merkato.com (Sep 19, 2026)
- Posted at: 2026-09-19T09:35:58.000Z
- Buyer website: https://natanimethiopia.org/
- Source: 2merkato