Textile, Garments and Uniforms
በልደታ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኝ ዳግም ህዳሴ ጤና ጣቢያ የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በልደታ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኝ ዳግም ህዳሴ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
- ሎት 1 የደንብ ልብስ የጨረታ ማስከበሪያ 4000 ብር
- ሎት 2 የፅዳት እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ 4000 ብር
- ሎት 3 እስቴሽነሪ እቃዎች የጨረታ ማስከበርያ 4000 ብር
- ሎት 4 የቋሚ የፈርኒቸር እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የጨረታ ማስከበርያ 7000 ብር
- ሎት 5 የህትመት ስራ የጨረታ ማስከበርያ 5000 ብር
- ሎት 6 መድሃኒት እና የህክምና እቃዎች ጨረታ ማስከበርያ 7000 ብር
- ሎት 7 የህንጻ እድሳት እና የፓርትሽን ስራ: lsolation ግንባታ፣ የጥበቃ ክፍል ግንባታ ስራ ሌሎችም የማስፋፋት ግንባታዎች ጨምሮ (የጥገና ግንባታ) ጨረታ ማስከበሪያ 7000 ብር
- ሎት 8 የጥገና እቃዎች ጨረታ ማስከበሪያ 4000 ብር
- ሎት 9 የመስተንግዶ ጨረታ ማስከበሪያ 1000 ብር
ስለዚህ ብቃት ያላቸውና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት የግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. ተጫራቾች ጨረታውን በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ አዲስ ልሳን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዳግም ህዳሴ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 409 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ ጋር ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዳግም ህዳሴ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 409 በመምጣት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ እዲሁም የጨረታ ማስከበርያ ሲፒኦ ከቴክኒክ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖረባቸዋል፡፡
5. ጨረታው ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛ ቀን በ4፡00 ሰዓት ዳግም ህዳሴ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ይከፈታል። የመክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥኑ ከመክፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት 1፣ ሎት 2፣ ሎት 3 የዕቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ሎት 4 ድርጅቱ የሚያቀርበውን እቃ በፎቶ እና ማኑዋል ዝርዝሩን በእስፔኩ መሰረት በፖስታ አሽጎ በሳምፕል መልክ ለግዢ ከፍል ማቅረብ አለበት እዲሁም እንደአስፈላጊነቱ የመስራያ ቤቱ ጥራት ኮሚቴ ድርጅታችሁ ባለበት ቦታ ሄዶ ዕቃውን የሚያይ ሆናል፡፡ በሎት 5 ደግሞ መስሪያ ቤቱ ሳምፕል በሚሰጠው መሰረት ዋጋ የሚሞላ ይሆናል በሎት 6 ተጫራች ባስገባው ዋጋ የሚወዳደር ሲሆን በሎት 7 ደግሞ ተጫራች መስራያ ቤቱ ባስቀመጠው ዲዛይን እና ቦታውን በአካል አይቶ ዋጋ የሚሞላ ይሆናል፡፡ በሎት 8 የዕቃዎች ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በድርጅቱ በሚያቀርበው ስፔስፊክሽን ሲሆን የተበላሹ ዕቃዎች ቦታው ድረስ በማየት ዋጋ የሚሞላ ይሆናል፡፡
7.ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባችዋል፡፡ አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዢ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
9. መስሪያ ቤቱ ለጨረታ ካቀረባቸው ዕቃዎች ውስጥ እስከ 20% ድረስ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ለእያንዳንዱ ዕቃ ዋጋ ከቫት ጋር ተሰርቶ መቅርብ አለበት
አድራሻ፡- በልደታ ክፍለ ከተማ ዳግም ህዳሴ ጤና ጣቢያ ከአባጅፋር መስጊድ ከፍ ብሎ መሰረተ ዕድገት ት/ቤት ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር፡- 011-2-79-13-59/ 011-2-79-14-80/
በልደታ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የዳግም ህዳሴ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-09-30
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-10-01 12:00
- Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Dagim Hidase Health Post
- Buyer address: በልደታ ክ/ከተማ ዳግም ህዳሴ ጤና ጣቢያ ከአባጅፋር መስጊድ ከፍ ብሎ መሠረት ዕድገት ት/ቤት ፊት ለፊት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Lessan (Sep 19, 2026)
- Posted at: 2026-09-19T08:43:26.000Z
- Source: 2merkato