Vehicle and Machinery Sale

ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ከባለእዳዎቹ ላይ ለሚፈልገው ገንዘብ በዋስትና የያዛቸውን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሐራጅ ማስታወቂያ

ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ከባለእዳዎቹ ላይ ለሚፈልገው ገንዘብ በዋስትና የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 ለባንኮችና ለማይክሮ ፋይናንስ በተሰጠው ስልጣን መሠረት ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች በመገንዘብ ማክበር ይኖርባቸዋል።

ንብረቱ አይነት / መኖሪያ ቤት

.

የተበዳሪዉ ስም

የመያዣ ሰጭዉ ስም

መኖሪያ/ የንግድ ቤት የሚገኝበት አድራሻ

የቦታው ስፋት በካሬ ሜትር

የንብረቱ አገልግሎት

የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር

የጨረታ መነሻ ዋጋ

ጨረታዉ የሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት፤

ጨረታው የሚከናወንበት ቦታ

1

ትዕዝብት አበበ

ብርሀኔ አበበ

በቂርቆስ /ከተማ፣ ወረዳ 03 የቤ. 712

149 ካሬ

መኖሪያ ቤት

AA00004 0801894/1

3,023,892 (ሶስት ሚሊዩን ሀያ ሶስት ስምንትመቶ ዘጠና ሁለት ብር)

መስከረም/11/ 2019 . ከጠዋቱ 400-5:00

አዲስ አበባ ዋናው መስሪያ ቤት

ተሽከርካሪ/ንብረቱ አይነት

.

የተበዳሪዉ ስም

የመያዣ ሰጭዉ ስም

የተሽከርካሪዉ ዓይነት እና የተመረተበት ዘመን

የሰሌዳ ቁጥር

የሻንሲ/ሴሪያል ቁጥር

የሞተር ቁጥር

የጨረታ መነሻ ዋጋ

ጨረታዉ የሚካሄድበት

ቀን

ሰዓት

1

መስከረም በላይነህ

መስከረም በላይነህ

አውቶሞቢል- ሊፋን ቀረጥ ተከፍሏል

አአ-03-B03589

LLV2A2A 14Coo63406

LF479Q3*1 20802285

250,000 (ሁለት መቶ ሀምሳ ብር )

ነሀሴ/21/2018 .

ከጥዋቱ 300- 4:00

2

ሚፍታህ አብዱረሃማን

በቃሉ ታዬ

ቮልስ ዋገን 2006 ቀረጥ ተከፍሏል

አአ-03-B64638

9BWCAO5 WO7T031982

ANZ250833

500,000 /አምስት መቶ ብር/

ነሀሴ/21/2018 .

ከጥዋቱ 400- 5:00

3

ሔዋን ዘላለም

ምስክር ሀይሉ

አውቶሞቢል ቶዩታ 2006 ቀረጥ ተከፍሏል

አአ-02-A90894

6TIBE33K X6X532235

*2AZ- A250299

1,000,000 (አንድ ሚሊዩን ብር)

ነሀሴ/21/2018 .

ከጥዋቱ 500-6:00

 

..

የንብረት ባለቤት

የተሽከርካሪዉ ዓይነት እና የተመረተበት ዘመን

የሰሌዳ ቁጥር

የሻንሲ/ሴሪያል ቁጥር

የሞተር ቁጥር

የጨረታ መነሻ ዋጋ

ጨረታዉ የሚካሄድበት

ሐራጁ የወጣበት ጊዜ

ቀን

ሰዓት

1

ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም .

ጃፓን ኒሳን አልሜራ/ ሚክራ-2017ቀረጥ ተከፍላል

አአ-03-A45189

MDHBBA M17Zo71119

HR1556319F

1,500,000/ አንድ ሚሊዩን አምስት መቶ /

ነሀሴ/21/2018 .

8:00-9:00

ለመጀመሪያ ጊዜ

2

ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም .

አውቶሞቢል ቶዩታ ዴክስ/1991 ቀረጥ ተከፍላል

አአ 03-78214

JT1EOE E9000396187

2E-2293339

350,000/ ሶስት መቶ ሀምሳ /

ነሀሴ/21/2018 .

9:00-10:00

ለመጀመሪያ ጊዜ

ማሳሰቢያ

1. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከነሀሴ 04 ቀን 2018 ጀምሮ እስከ ነሀሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ለተሸከርካሪዎች እንዲሁም እስከ መስከረም 08 ቀን 2019 ዓ.ም ደግሞ ለመኖሪያ ቤት ባሉት የስራ ቀናት በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ቀርቦ መውሰድ ይችላል።

2. ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የጨረታውን መነሻ ዋጋ ሀያ አምስት በመቶ (25%) የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲፒኦ በተቋሙ ስም በማሰራትና በማስያዝ አሊያም በጥሬ ገንዘብ በአካል ቀርቦ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

3. ከፍተኛ ዋጋ የሠጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከተቋሙ አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በፅኁፍ ሲደርሰው ነው።

4. የጨረታው አሽናፊ /ገዥ/ አሸናፊነታቸው ከተቋሙ በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ በአስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ በመክፈል ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል:: በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ንብረቱን ካተረከበ ንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ተቋሙ ኃላፊነት አይወስድም:: በተጠቀሱት ቀናት ቀሪውን ክፍያ አጠናቆ ከፍሎ ንብረቱን ባይረከብ ጨረታው ዉጤት ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ/ሲፒኦ/ ለተቋሙ ገቢ ሆኖ ጨረታው በድጋሚ ይካሄዳል:: በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ በእለቱ ይመለስላቸዋል።

5. የጨረታው አሸናፊ/ ገዢ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር ፣ በዋጋው ላይ የሚታሰብ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም፣ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ እና ሌሎች ወጪዎች ገዢ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮች ገዢው ይከፍላል።

6. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ሲመጡ ማንነታቸውን የሚገልፅ( የቀበሌ፤ የመንጃ ፈቃድ፤ እንዲሁም ብሄራዊ መታወቂያ) ተጫራቾች በህግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ህጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና መዝገባ ምስክር ወረቀት ሃራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ ይጠበቅበታል።

7. ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት የመያዣ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ የሚካሄድ ሲሆን ሌሎች ለውጦችን ተቋሙ በቅድሚያ ያሳውቃል:: ተበዳሪውና መያዣ ሰጪው በሐራጁ ቀንና ሰዓት በቦታው መገኘት ይችላሉ:: ነገር ግን ባይገኙ ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።

8. የተጫራቾች ምዝገባ ነሀሴ 20 ቀን 2018 ዓ/ም ለተሸከርካሪ መስከረም 08 ቀን 2019 ዓ/ም ደግሞ ለመኖሪያ ቤት ይጠናቀቃል።

9. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከተቋሙ ሕግ አገልግሎት ክፍል ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ከመካሄዱ ቀን 3 /ሶስት/ ቀናት አስቀድሞ መጎብኘት ይችላሉ።

10. ንብረቱ በገዢ ስም እንዲዞር ተቋሙ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል።

11. ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ አድራሻ፡- መገናኛ ለም ሆቴል አካባቢ፣ ኤልሳ ቆሎ አጠገብ በሚገኘው የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ህግ ክፍል በአካል ቀርቦ መጠየቅ ወይም በስልክ ቁጥሮች 011-668-43-82 / 011-618-55-10/ መደወል ይቻላል።

ሀርቡ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-21
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-09-21 16:00
  • Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Harbu Micro Finance S.C.
  • Bid bond: 25%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Reporter (Aug 09, 2026)
  • Posted at: 2026-08-10T14:20:16.000Z
← Back to all tenders