Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመጀመሪያ ዙር የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመጀመሪያ ዙር ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ሎት |
የሚገዛው የዕቃ አይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ በብር |
ምርመራ |
|
1 |
የፅህፈት ዕቃዎች |
10,000.00 |
|
|
2 |
የፅዳት ዕቃዎች |
10,000.00 |
|
|
3 |
የደንብ ልብስ |
10,000.00 |
|
|
4 |
ህትመት |
5000.00 |
|
|
5 |
የኪራይ አገልግሎት |
5000.00 |
|
|
6 |
የመስተንግዶ አገልግሎት |
5000.00 |
|
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታ እንዲሳተፉ ይፈልጋል፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው : የዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያለው፣ የንግድ ስም ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN NO/ ማቅረብ የሚችሉ እና ጨረታ መሳተፍ እንዲችሉ ከገቢዎች የተሰጣቸውን ታከስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለአንድ ሎት የማይመለስ ብር 150.00 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ ብቻ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000005067557 በየካ ክፍለ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም በማስገባት እና የከፈላችሁበትን ኦርጅናል ደረሰኝ በማቅረብ የጨረታ ሰነዱን ከየካ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ፋ/ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 14 መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT) ያካተተ እና የቀረበው ነጠላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ VAT ጨምሮ መሆኑን መግለጫ መስጠት አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች በእያንዳንዱ ዕቃ የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር በመግለፅ በታሸገ ኤንቨሎፕ ያቅራቢ ማህተም እና በዋጋ ማቅረቢያው ዝርዝር ላይ ዝርዝሩን የሞላው ኃላፊ በእያንዳንዱ ዋጋ በተሞላበት የጨረታ ሰነድ ላይ በየገጹ በመፈረም ለዚህ ተብሎ የተዘጋጀውን የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዋናውንና ኮፒውን በተለያየ ፖለታ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ኦርጅናል ደረጃውን የጠበቀ ናሙና በየካ/ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት ማስረከብ አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ስትመልሱ ሙሉ አድራሻችሁን በተሰጠው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በትክክል መሙላት ይኖርባችኋል፡፡
7. ተጫራቾች ያሸነፏቸውን ዕቃዎች ተወዳድረው ካሸነፉ በኋላ ከቀረበው ናሙና ምንም ለውጥ ሳያደርጉ በራሳቸው ወጪ ጭነው የማምጣት ግዴታ አለባቸው፡፡
8. ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋት በ3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
9. የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በጽሁፍ የሚገለጽላቸው ሲሆን ለጨረታው አፈፃፀም ውል ማስከበሪያ ለአሸነፉበት ጠቅላላ ዕቃ ዋጋ 10% CPO በማስያዝ ውል የመዋዋል ግዴታ አለባቸው፡፡
10. ከፍያው የሚፈፀመው ለሚያቀርቡት ዕቃ ሙሉ በሙሉ በናሙና መሰረት ጥራቱ ሲረጋገጥ እና በንብረት ክፍል ገቢ ሲሆን ብቻ ነው::
11. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ብቻ መግለፅ ወይም መሙላት አለባቸው፡፡
12. የጨረታ ማስረከቢያና የውል ማስከበሪያ ደብዳቤ የምታጽፉ ጥቃቅንና አነስተኛ አቅራቢዎች የተሰማራችሁበትን የንግድ ስራ መስክ ዘርፍ የሚገልጽ ደብዳቤ ካደራጃችሁ ተቋም ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
13. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ቢበዛ ለ60 ቀናት ብቻ ነው::
14. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0116 660 974 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ልዩ ቦታ ኮተቤ 02 ወደ ህዝብ ደህንነት እና አንቆርጫ መውጫ ወረዳ 10 ጤና ጣቢያ ፊት ለፊት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-21
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋት በ3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-21 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Yeka Sub City Administration Woreda 10 Finance Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 150.00 ብር ለአንድ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Aug 10, 2026)
- Posted at: 2026-08-11T07:39:59.000Z