Stationery
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 03 ፋይናንስ ፅ/ቤት የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
StationeryOffice Supplies and ServicesEquipment and Accessories
Addis Ababa
More tags
Electrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesTextile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherCleaning and Janitorial Equipment and ServiceSpare Parts and Car Decoration MaterialsSport Materials and EquipmentPharmaceutical ProductsHealth Care, Medical IndustryProducts and ServicesAgriculture and FarmingRaw Materials and SuppliesOffice FurnitureFurniture and FurnishingHouse FurniturePrinting and PublishingPrinted Advertising MaterialsAdvertising and PromotionTransportation ServiceWarehousing, Transit and Transport ServiceFreight TransportVehicleRentTour and TravelHospitality, Tour and TravelShoes and Other Leather ProductsTri Wheeler, Motorcycles and Bicycles PurchaseAmharic2merkatoKolefe Keranio Sub City Administration Woreda 03 Finance Office
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ 1ኛ ዙር ቁጥር 001
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 03 ፋይናንስ ፅ/ቤት ከዚህ በታች በሎት የተደራጁ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች እና ሌሎች
- ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት 3 የደንብ ልብሶች
- ሎት 4. የጽዳት እቃዎች ስፖርት መገልገያ እቃዎች የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማ
- ሎት 5. መድሃኒት እና የተለያዩ ዘሮች
- ሎት 6. የቋሚ እቃዎች
- ሎት7. ህትመትና ሌሎች
- ሎት 8. የትራንስፖርትና ጭነት አገልግሎት
በመሆኑም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ካራ ቆሬ የሚገኘው ህንፃ ቀርበው መውሰድ እንደሚችሉ እናሳውቃለን።
ተጫራቾች ማሟላት የሚኖርባቸው።
- የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የአስገቡት ዋጋ ለሁሉም ሎት 1.5 % በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ ከተደራጁ ሲፒኦ ማስያዝ አይጠበቅባቸውም በምትኩ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው። የሚቀርበው ደብዳቤ በኃላፊ መፈረም አለበት።
- የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው የሚቀርበው የዋጋ ሰነድ ለቫት ተጠቃሚዎች ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
- ትራንስፖርት ላይ ለሚወዳደሩት የተሽከርካሪ ባለቤትነት መታወቂያ ወይም ሊብሬ ኮፒ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ከትራንስፖርት ውጪ ማንኛውም ተጫራች የታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱ ማህተም መኖር አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ሰነድ ኮፒና ዋና ማቅረብ ይኖርበታል።
- ለሎት 8 ብቻ ማሟላት የሚገባውን ሰነድ ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ከሆኑ የሚበረታታ ሲሆን ይህን ማቅረብ ካልተቻለ በምትኩ ቲኦቲ ወይም 2% ከፋይ መሆን ይኖርበታል።
- አሸናፊ ተጫራች በሰነድ ውስጥ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ ቀርቦ ውል መዋዋል አለባቸው።
- የእቃ ማስረከቢያ ቦታ ወረዳ 03 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ይሆናል።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ያላቀረበ ድርጅት ከውድድር ውጪ ይሆናል። እቃው በናሙናው ላይ ያለውን የጥራት ደረጃ ይዞ ካልተገኘ ተመላሽ ይደረጋል።
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች በማቅረብ ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን እቃዎች በወቅቱ ማቅረብ ካልቻሉ ያስያዙት ሲፒኦ ይወረሳል።
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉበትን እቃ 10% ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊ ድርጅት ውል ከገባበት ቀን ጀምሮ በ10 (አስር ) ቀን ውስጥ እቃውን ማቅረብ ይኖርበታል።
- አንድ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም።
- የጨረታው ሳጥን ጨረታው አየር ላይ ከዋለ ከ10 የስራ ቀን በኋላ በአስራ አንደኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ውስጥ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ቦታው ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች (በጨረታው) የተሸነፉ ድርጅቶች የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይሆናል። ጽ/ቤቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ
መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ልዩ ቦታ ካራ ቆሬ ሩታ ከግራር 200 ሜትር ገባ ብሎ ወረዳ 03 ፋይናንስ ጽ/ቤት መሆኑን እንገልጻለን።
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 03 ፋይናንስ ፅ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-21
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): የጨረታው ሳጥን ጨረታው አየር ላይ ከዋለ ከ10 የስራ ቀን በኋላ በአስራ አንደኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-21 10:30
- Bid opening (note): የጨረታው ሳጥን ጨረታው አየር ላይ ከዋለ ከ10 የስራ ቀን በኋላ በአስራ አንደኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Kolefe Keranio Sub City Administration Woreda 03 Finance Office
- Bid bond: ለሁሉም ሎት 1.5 %
- Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎት 200(ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 10, 2026)
- Posted at: 2026-08-11T07:43:21.000Z