Equipment and Accessories

በአርሲ ዞን ሙኔሳ ወረዳ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ የመኪና ጎማዎች እና ለሙኔሳ ቲቪት ኮሌጅ የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁ.01/2019

በአርሲ ዞን ሙኔሳ ወረዳ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የፅህፈት መሣሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ፣ የመኪና ጎማዎች እና ለሙኔሳ ቲቪት ኮሌጅ የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

1. ለተጠየቁ የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (tax payer Registration No.) የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ እና በፌዴራል፣ ክልል ወይም ዞን በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጄንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

2. ተጫራቶች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ ለፅህፈት መሳሪያዎች እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ብር ቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች ብር 500.00 (አምስት መቶ) ለፅዳት እቃዎች እና ለደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ለሙኔሳ ወረዳ የሚውሉ ማሽነሪዎች Wood Mizer model LT 70, Jointer Machine model Mb 505, Sliding Table Saw machine model MJ6132D/MJ6128B and Thickness planer machine model S 500 ለጨረታ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በሙኔሳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም ሲንቄ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1055513580213 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ፅ/ቤት ግዢ ፤ ንብረት አስተዳደር ማስወገድ ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች በግብር ሰብሳቢው ጽ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡

4. ተጫራቶች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በግዢ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ 16ኛ የስራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ተጫራቶች በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚህ ዕለት ከቀኑ በ4፡30 ሠዓት ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የፋይናንስ ሃላፊ ቢሮ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡

5. ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፤ ለፅህፈት መሳሪያዎች እና ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስረከቢያ ብር 20000 (ሃያ ሺ ብር) ለአንድ ልብስ ሰነድ ጨረታ ማስረከቢያ ብር 25000 (ሃያ አምስት ሺህ ብር) ለፅዳት እቃዎች 20000 (ሃያ ሺ ብር) ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች ሰነድ የጨረታ ማስረከቢያ ብር 20000 (ሃያ ሺ ብር) እንዲሁም ለሙኔሳ ወረዳ ቲቪት ኮሌጅ የሚውሉ ማሽነሪዎች ሰነድ የጨረታ ማስረከቢያ ብር 20000 (ሃያ ሺህ ብር) በአቅረቢያቸው በሚገኙ የታወቀ ባንክ ከፍያ ማዘዣ ብቻ ማቅረብ፡፡

6. አሸናፊ ተጫራቾች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዝ ወጪ ቀርሳ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡

7. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁጥር 09-13-89-50–94 / 09-11-94-05-73

የአርሲ ዞን ሙኔሳ ወረዳ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-27
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ 16ኛ የስራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ተጫራቶች በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-27 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ 16ኛ የስራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ተጫራቶች በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ4፡30 ሠዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Munesa Woreda Finance Economic and Development Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 10, 2026)
  • Posted at: 2026-08-11T07:51:47.000Z
← Back to all tenders