Cleaning and Janitorial Equipment and Service

አልፋ መስማት የተሳናቸው ልዩ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019

አልፋ መስማት የተሳናቸው ልዩ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ................2850.50
  • ሎት 2. የጽዳት እቃ..............1260.50
  • ሎት 3. የደንብ ልብስ.......................2803.62
  • ሎት 4. የስፖርት እቃ............1769.70
  • ሎት 5. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች...........2576.52
  • ሎት 6. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች............5000.00
  • ሎት 7. ፈርኒቸር..........2709.00

ስለሆነም ተጫራቾች

1. ለተጠቀሱት እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው። እንዲሁም የንግድ መለያ ቁጥር (Tin Number) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የማይመለስ 200.00 (መቶ ብር) በመክፈል የጨረታው ሠነድ ከት/ቤቱ ፋይናንስ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2% ከላይ በየሎቱ የተገለጸውን የብር መጠን በባንክ በተመሰከረ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።

7. ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከ10ኛው የስራ ቀን ቀጥሎ ባለው አስራ አንደኛው ቀን 4:00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል።

8. አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

9. ት/ቤቱ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. አሸናፊ በራሱ ትራንስፖርትና ወጭ ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች የት/ቤቱ ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋል።

11. ማንኛውም ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

12. ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉት እስቶር ውስጥ ወይም መጋዘን ባላችሁ እቃ ላይ ሊሆን ይገባል።

13. በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

14. ብዛቱ ሊጨምርም ሆነ ሊቀንስ የሚችለው በመቶኛ 20% ይሆናል።

አድራሻ፡- ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ከጃፓን ኢምባሲ 250 ሜትር ገባ ብሎ

ስልክ፡- 011 618 3496

አልፋ መስማት የተሳናቸው ልዩ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-20
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-08-21 10:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ከ10ኛው የስራ ቀን ቀጥሎ ባለው አስራ አንደኛው ቀን 4:00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Alpha Special School for the Deaf
  • Buyer address: ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ከጃፓን ኢምባሲ 250 ሜትር ገባ ብሎ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 11, 2026)
  • Posted at: 2026-08-11T08:56:54.000Z
← Back to all tenders