Cleaning and Janitorial Equipment and Service

የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር በ2019 በጀት ዓመት በ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማሰራት/ ይፈልጋል

Description

የ2019 ዓ.ም አንደኛ ዙር የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር በ2019 በጀት ዓመት በ1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን

  • ሎት 1 አላቂ እቃ /እስቴሽነሪ/
  • ሎት 2 የጽዳት እቃ፣
  • ሎት 3 የደንብ ልብስ፣
  • ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ
  • ሎት 5 ዲኮርና ሞንታርቦ ኪራይ፣
  • ሎት 6 ህትመት
  • ሎት 7 መኪና ኪራይ፣
  • ሎት 8 መስተንግዶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማሰራት/ ይፈልጋል።

1. በዚህም መሠረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ፤

2. የንግድ ፈቃድ ምስክር ወረቀት

3. የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት

4. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

5. የቫት ተመዝጋቢ የምስከር ወረቀት የሚያቀርቡና የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ለዚህም ማስረጃ

6. ነጋዴዎች በነጋዴዎች ዌብሳይት ላይ ስም ዝርዝራቸው ለመኖሩ ፕሪንት አውት ማቅረብ አለባቸው።

7. በሚያስገቡት ሰነድ ላይ የድርጅቱን ክብ ማህተም መምታትና መፈረም ስርዝ ድልዝ የተደረገ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

8. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር በየሎቱ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ብር በመከፈል የካ አለባቸው ከፍለ ከተማ ወረዳ 05 ፋይናንስ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ መውሰድ ይችላሉ።

9. የሚያቀርቡት እቃ ዋጋ ከብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ማቅረብ

10. በአነስተኛና ጥቃቅን የምትወዳደሩ ነጋዴዎች የምታስገቡት የድጋፍ ደብዳቤ ለሀገር ውስጥ ምርትና ደብዳቤ የማናስተናግድ መሆኑን አምራችነታችሁን የሚገልጽ መሆን እንዳለበት እያሳወቅን፤ ከሀገር ውጪ ለሚመረቱ ለሚገቡ ምርቶች በድጋፍ

11. በጨረታ ላይ ያጣናቸው እቃዎች በሙሉ ኦሪጅናል እና ጥራታቻውን የጠበቁ መሆን አለባቸው።

12. ተጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ፖስታ በሚያስገቡበት ጊዜ ለሚያቀርቡት እቃ ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው የተወዳደሩበት እቃም በእስቶራቸው ውስጥ አስቶክ ያላቸው መሆን አለባቸው፣ ከዚህ ውጪ እስቶክ በሌላቸው እቃ ተወዳድረው አሸናፊ መሆናቸውን ሲያውቁ ዋጋ ጨመረ በሚል ሰበብ አናቀርብም በሚሉ ነጋዴዎች ላይ ምክንያቱን የማንቀበል እና ቀጥታ ወደ ክስ የምንሄድ መሆኑን እናሳውቃለን።

13. ተጫራቾች ያሸነፏቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወረዳው ድረስ ማምጣት አለባቸው።

14. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ብቻ የሚወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን በመጨመር የቴክኒክና ፋይናንሽያል ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በሁለት ፖስታ በማሸግ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ውስጥ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ፋይናንስ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

15. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን የሚያሲዙት በየሎቱ ሲሆን ለአንድ ሎት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

.

ሎት

የእቃው ዓይነት

CPO

የጨረታ ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን

ብር

ሳን

1

ሎት 1

አላቂ እቃ

CPO ማስያዣ

 25,000

 00

2

ሎት 2

የፅዳት እቃ

CPO ማስያዣ

 25,000

 00

3

ሎት 3

ደንብ ልብስ

CPO ማስያዣ

 25,000

 00

4

ሎት 4

ኤሌክትሮኒክስ

CPO ማስያዣ

 10,000

 00

5

ሎት 5

ህትመት

CPO ማስያዣ

 6000

 00

6

ሎት 6

ዲኮርና ሞንታርቦ ኪራይ

CPO ማስያዣ

 11,000

 00

7

ሎት 7

መስተንግዶ

CPO ማስያዣ

 15,000

 00

8

ሎት 8

ቋሚ እቃ

CPO ማስያዣ

 25,000

 00

9

ሎት 9

የትራንስፖርት

CPO ማስያዣ

 11,000

 00

16. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን እቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከጽ/ቤቱ ጋር በ15 ቀን ውስጥ የግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል፤ በመሆኑም 10% የውል ማስከበሪያ ያስገቡበትን ደረሰኝ ሳያወጡ እቃውን ብቻ የሚያመጡ ነጋዴዎችን የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

17. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምር ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ተዘግቶ በእለቱ 3፡30 የሚከፈት ሲሆን በጨረታው አከፋፈት ላይ ለመገኘት ፍላጐት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው አስተዳደር ግቢ ውስጥ ይከፈታል።

18, መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

19. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።

አድራሻ፡-

መገናኛ ከዲያስፖራ አደባባይ ወደ ኮተቤ በሚወስደው መንገድ ቶፕ ቪው አጠገብ የካ ተራራ ት/ቤት ፊት ለፊት ያለው የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት

ለመረጃ ስልጥ ቁጥር 09 11 78 71 70/ 09 31 50 30 48/ 09 10 92 36 95

በየካ ክ/ከተማ የወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-21
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00
  • Bid opening: 2026-08-21 09:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Yeka Sub City Woreda 5 Administration Finance Bureau
  • Buyer address: መገናኛ ዲያስፖራ አደባባይ ወደ ኮተቤ በሚወስደው መንገድ ቶኘ ቪው አጠገብ የካ ተራራ ት/ቤት ፊት ለፊት ያለው የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር በየሎቱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 10, 2026)
  • Posted at: 2026-08-11T09:22:20.000Z
← Back to all tenders