Textile, Garment and Leather

በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/10 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም የ1ኛ ዙር ጨረታ የተለያዩ እቃዎች እና ተያያዥ አገልግሎቶችን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም

በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/10 ፋይናንስ ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም የ1ኛ ዙር ጨረታ የተለያዩ እቃዎች እና ተያያዥ አገልግሎቶችን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት

  • ሎት 1፡ የሰራተኞች ደንብ ልብስ
  • ሎት 2፡ የቢሮ አላቂ እቃዎች እና ጽህፈት መሳሪያዎች
  • ሎት 3፡ የጽዳት እቃዎች
  • ሎት 4፡ ኤሌክትሮኒክ እቃዎች ጥገና
  • ሎት 5፡ ቋሚ እቃዎች ግዥ
  • ሎት 6፡ ህትመት ውጤቶች
  • ሎት 7፡ ትራንስፖርት (የመኪና ኪራይ)
  • ሎት 8፡ መስተንግዶ አቅርቦት
  • ሎት 9፡ የዲኮር ኪራይ፣ የጀኔሬተር ኪራይ፣ የሞንታርቦ ኪራይ እና የድንኳን ኪራይ
  • ሎት 10፡ የጉልበት ስራዎች ኢሌክትሪክ ስራዎች የፈርኒቸር እቃዎች ገጠማ ስራ እና ጥገና ስራዎች
  • ሎት 11፡ የኔትወርክ ስራ እና የስልክ ዝርጋታ ስራዎች
  • ሎት 12፡ የመኪና እቃዎች ግዥ እና የመኪና ጥገና አገልግሎት
  • ሎት 13፡ የዶሮ ግዥ እና ፓኬጅ ግዥ
  • ሎት 14፡ የህንጻ ቀለም ቅብ፣ የደረጃ መወጣጫ መደገፊያ ብረት ብየዳ ስራ እና የጥበቃ ቤት እድሳት ጥገና ስራ

ከላይ የተጠቀሱትን እቃዎች አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾችን ከሎት1-6 እና 8 እና 13 ለተጠቀሱት እቃ ተያያዥ አገልግሎቶች በመስኩ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ vat ተመዝጋቢ የሆኑ ፤ አቅራቢነትና TIN no ከጨረታ ሰነዱ ጋራ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል ነገር ግን ሎት 7 እስከ 14 የሚያቀርቡ ድርጅቶች ግለሰቦች ከላይ ከተጠቀሱ መስፈርቶች በተጨማሪ ቫት ወይም ቲ.ኦ.ቲ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ኮ/ቀ/ወ/ 10 ፋ/ጽ/ቤት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በየሎቱ የማይመለስ 300.00 / ሶስት መቶ ብር ከፍለው በመውሰድ የእቃዎች ዝርዝር ዋጋ ቫትን ጨምረው በመሙላት ኦርጂናል እና ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ ፖስታ በተዘጋጀው ሳጥን ገቢ ማድረግ አለባቸው።

የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል።

ተጫራቾች መስሪያ ቤቱ በሸጠላቸው መደበኛ የጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው መመለስ የሚኖርባቸው ሲሆን የእቃውን ዝርዝር ሞልቶ ለመላክ ቦታ ያንሳል ካሉ በተጨማሪ በራሳቸው ወረቀት በመሙላት የሃላፊ ፊርማና ህጋዊ የድርጅቱ ማህተም በማድረግ ወረዳው ከሸጠላቸው ሰነድ ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ሰነድ ላይ ስልጣን ባለው አካል የተፈረመባቸው የተሟላ አድራሻቸውን የሚገልጽ ህጋዊ ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የጨረታ ሰነዱ ሙሉ ክፍል አብሮ የሚመለስ ይሆናል ተጫራቾች በሚያቀርቡት የእቃ ዋጋ የእቃው ዓይነት /ብራንድ/ እቃው የተመረተበት ሀገር በግልጽ የተጠቀሰ መሆን አለበት። እንዲሁም ጨረታው ከመከፈቱ በፊት እቃዎች ናሙና ኦርጂናል/ትክክለኛነት/ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።በተጨማሪም መስሪያ ቤቱ በሚቀርበው ናሙና መሰረት ማቅረብ አለባቸው።

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ የተከፋፈለ ሲሆን

  • ሎት 1፣ 10,000(አስር ሺህ ብር)
  • ሎት 2፣ 10,000(አስር ሺህ ብር)
  • ሎት 3፣ 8000 (ስምንት ሺህ ብር)
  • ሎት 4፣ 5000/ አምስት ሺህ ብር/
  • ሎት 5፣ 10,000 (አስር ሺህ ብር)
  • ሎት 6፣ 5000 /አምስት ሺህ
  • ሎት 7፣ 8000 (ስምንት ሺህ ብር)
  • ሎት 8፣ 5000(አምስት ሺህ ብር)
  • ሎት 9፣ 4000(አራት ብር)፤
  • ሎት 10 2000 (ሁለት ሺህ ብር)፤
  • ሎት 11 3000 (ሶስት ሺህ ብር)፤
  • ሎት 12፣ 6000 (ስድስት ሺህ ብር፣)፤
  • ሎት13፣ 10,000 (አስር ሺህ ብር) ፤
  • ሎት 14፣ 10,000 (አስር ሺህ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

መስሪያ ቤቱ አሸናፊ ተጫራቾች ከመረጠ በኋላ ከሚገዙት እቃዎች ብዛት መጠን ላይ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 25 ፐርሰንት የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ የዋጋ ለውጥም ሆነ ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም።

በተወዳደሩበት ዋጋ አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው በኋላ በ 7 ቀናት ውስጥ ቀርበው የውል ማስከበሪያ 10 ፐርሰንት ለግዢ ፈፃሚው አካል ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ያስያዙት ገንዘብ ተመላሽ የሚሆነው በውል መሰረት የሚጠበቅባቸውን ግዴታ ከተወጡ ውሉን ተመላሽ ሲያደርጉ ነው።

ተጫራቾች ሌላው ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡ በጨረታው ያሸነፉ ወይም ተጫራቾች ያሸነፉበትን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት፣መጫኛ እና ማውረጃ ወጪ ጨምሮ በወረዳ 10 ፋይናንስ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ የሚያቀርቡ ይሆናል።

መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

በጥቃቅን የተደራጁ አካላት ከሆኑ ሰነድ ለመውሰድ በሚመጡበት ጊዜ ከሚመለከተው አካል ወቅታዊ የሆነ በጽ/ቤቱ ስም፣የጨረታ ቁጥሩን እና ከላይ ከሎት 1-14 በተገለፀው መሰረት የእቃን ወይም የአገልግሎቱን አይነት የሚገልጽ ባደራጃቸው ጽ/ቤት ሃላፊ ፊርማ የተፈረመ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።

በተጨማሪ በጥቃቅን የተደራጁ ድርጅቶች አምራች የሆኑ ብቻ ይሆናሉ። በተባለው መሰረት ያላቀረቡ ድርጅቶች የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፤ ሁሉም የሚቀርቡ ሰነዶች ሌሎቹም በአማርኛ የተፃፉ መሆን አለባቸው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0112739258/ በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወረዳ 10 ፋ/ጽ/ቤት18 ማዞሪያ በተስምዶ መላጣ ሜዳ የሚባስው ከመብራት ሀይል ከፍ ብሎ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 ላይ ይገኛል።

በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የወረዳ 10 ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-22
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-22 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Kolfe Keraniyo Sub City Wereda 10 Finance Bureau
  • Buyer address: 18 ማዞሪያ በተለምዶ መላጣ ሜዳ የሚባለው ከመብራት ኃይል ከፍ ብሎ ምድር ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በየሎቱ 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 11, 2026)
  • Posted at: 2026-08-11T09:57:59.000Z
← Back to all tenders