Cleaning and Janitorial Equipment and Service

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የአንደኛ ዙር በወረዳው ለተለያዩ ጽ/ቤቶች ለስራ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎች እና አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት(ማሳተፍ) ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 001-2019 ዓ.ም

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የአንደኛ ዙር በወረዳው ለተለያዩ ጽ/ቤቶች ለስራ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የደንብ አልባሳት፣ የተለያዩ የጭነትና የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስና የፈርኒቸር ጥገና አገልግሎት፣ የሞንታርቦ እና የጄኔሬተር ኪራይ አገልግሎት፣ የዲኮር ኪራይ አገልግሎት፣ የህትመት አገልግሎት፣ የግንባታ ስራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት(ማሳተፍ) የሚፈልግ ሲሆን

.

የዕቃ ኮድ

የዕቃው ዓይነት

 

የብር መጠን

1

6212

የተለያዩ የፅህፈት መሳሪዎች

ናሙና የሚቀርብበት

25,000

2

6218

የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች

ናሙና የሚቀርብበት

25,000

3

6211

የተለያዩ የደንብ አልባሳት

ናሙና የሚቀርብበት

25,000

4

6252

የጭነት መኪና

መስሪያ ቤቱ በሚፈልገው ሰዓት የሚገኝ

15,000

5

6243

የኤሌክትሮኒክስና የፈርኒቸር ጥገና

በሙያው ብቁ ልምድ ያለው

15,000

6

6252

የሞንታርቦ የጄኔሬተር ዲኮር

የተሟላ ዕቃ ያለው እና ማቅረብ የሚችል

10,000

7

6255

የጉልበት ሰራተኛ ኪራይ

መስሪያ ቤቱ በሚፈልገው ሰዓት የሚገኝ

1000

8

6244

የግንባታ ስራ

መስሪያ ቤቱ በሚያዘው ዲዛይን መሰረት

15,000

ስለዚህ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው

1. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው እና በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው ይመልከቱ የሚል በጽሁፍ ማቅረብ አለባቸው

2. የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ

3. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው

4. በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ የሚችልና በወቅቱ በማንኛውም ሁኔታ ያልተቀጣ (እንዳይወዳደር ያልታገደ) መሆን አለበት

5. በዚህ ጨረታ አማራጭ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም

6. በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በሰንጠረዥ በተጠቀሰው የብር መጠን መሰረት በቢልቦንድ ሲ.ፒ.ኦ ቼክ 2% በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል

7. አሸናፊነታቸው ከተገለፀላቸው በኋላ ለውል ማስከበር የ10% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን (ፋይናንሺያል) ሰነዶችን በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ ማቅረብ አለበት በየሎቱ ያስገቡትን የዋጋ መጠን ጠቅላላ ድምር ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል

8. ፖስታ ስታስገቡ በየሎቱ ለይታችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል ለምሳሌ 6212 በአንድ ፖስታ 6211 በሌላ ፖስታ 6218 በሌላ ፖስታ ሁሉም ሎቶች በተለያዩ ፖስታ ማስገባት በጠበቅባችኋል

9. ማንኛውም ተጫራች የሚያስገባው ሰነድ የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ፣ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን

10. በጨረታው አሸነፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን በራሳቸው ትራንስፖርት የካ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት ልዩ ቦታው ፈረንሳይ ለጋሲዮን 41 እየሱስ መሄጃ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው የጽ/ቤት ግምጃ ቤት ወይም ንብረት ክፍል 6 በፍላጎት መግለጫው በተጠቀሰው የማስረከቢያ ቦታ ድረስ በመምጣት ማስረከብ አለባቸው

11. በጨረታ ሰነድ ክፍል 6 ውስጥ በሚገኘው የፍላጎት መግለጫ ላይ በተገለፀው መሰረት ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነዶች ተገምግመው አሸናፊው ያሸነፈባቸውን የፅህፈት መሳሪያዎች የጽዳት ዕቃዎች የደንብ አልባሳት እንዲሁም ከላይ በጨረታ የተገለፁትን እቃዎች ሙሉ ለሙሉ አዘጋጅተው ገቢ ከማድረጋቸው በፊት ከእየአይነቱ ናሙና ማቅረብ አለበት

12. ተጫራቾች የካ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት ልዩ ቦታው ፈረንሳይ ለጋሲዮን 41 እየሱስ መሄጃ በሚወስደው አስተዳደር ግዥ የስራ ሂደት ቀርበው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) ከፍለው መግዛት ይችላሉ

13. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 – 11፡30 ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ በወረዳው ግዥ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 21 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል

14. በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ3፡30 የሚከፈት ሲሆን በመስሪያ ቤቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል

15. የጨረታው መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ሰዓት የሚከፈት ይሆናል

16. ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ሰነድ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን

17. መ/ቤቱ የተሻለ መንግድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011 154 8607 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

አድራሻ፡- የካ/ክ/ከ ወረዳ 01 ፋ/ጽ/ቤት ፈረንሳይ ለጋሲዮን ወደ 41 እየሱስ በሚወስደው መንገድ

በየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 01 ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-22
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-22 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Yeka Sub City Woreda 01 FEDB
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 11, 2026)
  • Posted at: 2026-08-11T10:39:48.000Z
← Back to all tenders