Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በም/ወለጋ ዞን የሆማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ/ም ለሆማ ወረዳ ለተለያዩ የመንግስት መ/ቤቶች የተለያዩ የቢሮ አላቂ እና፣ ቋሚ እቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ደንብ ልብሶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለሴክተር መስሪያ ቤቱ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በም/ወለጋ ዞን የሆማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ/ም ለሆማ ወረዳ ለተለያዩ የመንግስት መ/ቤቶች የተለያዩ የቢሮ አላቂ እና፣ ቋሚ እቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ ፋርኒቸሮች፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ደንብ ልብሶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለሴክተር መስሪያ ቤቱ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ እና በተወዳዳሪዎች መማሪያ መሠረት ተጫራቾች ቀርበው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።
የጨረታ መስፈርቱ፣
1. ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች ማቅረብ የሚችሉና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤
2. በመንግሥት ጨረታዎች መሳተፍ የሚያሰችል የምዝገባ ምስክር ወረቀት አግባብ ካለው ህጋዊ አካል ማቅረብ የሚችሉ፤
3. የ2018 ዓ/ም ግብር አጠናቅቆ የከፋሉበትን ማስረጃ የሚያቀርቡና ለታክስ ከፋይነት (TIN) የተመዘገቡ እና ተጨማሪ ታክስ (VAT) ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ፤
4. ለጨረታ መስከባሪያ ጠቅላለ ካቀረቡት ዋጋ 3% በተረጋገጠ (CPO) ከማስረጃቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣባት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት(15)የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር (200) በመክፈል ከግዥ ክፍል መግዛት ይችላሉ፤
6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን በሆማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለዛው ለተዘጋጄው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
7. ተጫራቾች የሚወዳዳሩበት የዕቃ ዓይነት የቢሮ ዕቃ መሆኑን እንደዚሁም የድርጅቱን ስም በሚያቀርቡ የተለያየ ፖስታ ላይ በኦሪጅናሉ እና በኮፒው በግልጽ በመጻፍ በድርጅቱ ማሕተም እና ፊርማ አስደግፈው ማቅረብ አለባቸው፤
8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በተለያየ ኤንቬሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
9. ተወዳደሪዎች ናሙና እንዲያቀርቡባቸዉ የተጠየቁትን ሙሉ በሙሉ ማቅረብ እና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ቆጥሮ ማስረከብ አለባቸው፤
10. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣባት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛዉ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
11. ተጨራቾች በጨረታዉ አሸናፊ ሲሆኑ ዕቃዎቹን በራሳቸው ማጓጓዣ እስከ ገዥው ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፤
12. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09-24-96-73-46 ወይም 09-66-50-75-61 መጠየቅ ይችላሉ፤
13. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ከአገኘ ጨረታውን በከፍል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሆማ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-27
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት(15) የስራ ቀናት
- Bid opening: 2026-08-28 12:00
- Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣባት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛዉ የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: West Wollega Zone Homa Woreda FEDB
- Bid bond: 3%
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
- Published on: Addis Zemen (Aug 11, 2026)
- Posted at: 2026-08-11T10:53:35.000Z