House and Building Sale
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት ንብረቶችን በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የዝግ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሠረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከባቸውን እና ቀደም ሲል በሐራጅ ወጥተው ሳይሸጡ የቀሩትን ከዚህ በታች በሠንጠረዡ የተዘረዘሩትን ንብረቶች በዝግ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
1. የሚሸጡ ንብረቶች ዝርዝር
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው / የመያዣ ሰጪው ስም |
ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ |
የሚሸጠው ንብረት አይነት |
የመያዣ ንብረት ዝርዝር መረጃ |
የቀሪ ሊዝ ዘመን |
የጨረታው መነሻ ዋጋ (ብር) |
የጨረታው ደረጃ |
ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ፣ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ደሳለኝ መብራቱ እርሻ ልማት ድርጅት |
በጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/ መንግስት፣ ኢታንግ ልዩ ወረዳ፣ አኛሌ ቀበሌ |
የእርሻ መሬት |
402 ሄክታር ጠቅላላ መሬት (ከዚህ ውስጥ 207.40 ሄክታር የለማ)። |
34 ዓመት |
9,903,189.28 (ዘጠኝ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሦስት ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ብር ከ28 ሳንቲም) |
ዝግ ጨረታ |
ጋምቤላ ዲስትሪክት ጽ/ቤት፣ ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
|
ሕንፃዎች |
የሠራተኛ የመኖሪያ፣ ቢሮዎች፣ መጋዘን፣ እና የመፀዳጃ ቤት ግንባታዎች ያሉት። |
|||||||
|
የእርሻ ትራክተር |
አንድ ሜሲ ፈርጉሰን (Massey Ferguson) ትራክተር፤ ሞዴል MF460፤ የ2014 ምርት፣ የብራዚል ምርት የሆነ። |
2. የጨረታው መመሪያ
1. ተወዳዳሪዎች የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በፎርማቱ ላይ በመጥቀስ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ዓላማ በባንኩ ጋምቤላ ዲስትሪክት ጽሕፈት ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:50 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ / CPO) ብቻ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስም በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ።
3. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 (አሥራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ በባንኩ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ አለበት። ይህ ካልሆነ ግን ያስያዘው CPO ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።
4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሠንጠረዡ በተመለከተው ቀንና ሰዓት በጋምቤላ ዲስትሪክት ጽሕፈት ቤት ይካሄዳል። ሕጋዊ ሰውነት ያላቸውን አካላት ወክለው የሚቀርቡ ሰዎች የመሥራች ጽሑፍ፣ የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፈቃድ እና የተረጋገጠ ውክልና ሰነድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና ሌሎች ሕጋዊ ክፍያዎችን (ካለ) ገዢው ይከፍላል።
6. አንዳንድ የድርጅቱ ንብረቶች (ለምሳሌ ትራክተሩ) ከቀረጥ ነፃ የገቡ ሊሆኑ ስለሚችሉ፣ ገዢው ተመሳሳይ የቀረጥ ነፃ መብት ያለው ወይም የሚፈለገውን ቀረጥ ለመከፈል የሚስማማ መሆን አለበት።
7. የጨረታው አሸናፊ የባንኩን የብድር መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ ባንኩ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ከፊል ብድር (ዱቤ ሽያጭ) ሊመቻችለት ይችላል።
8. የንብረቱ ስም ወደ ገዢው እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግሥታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል፤ ገዢው ጉዳዩን ተከታትሎ ያስፈጽማል።
9. ተጫራቾች ንብረቱን መጎብኘት የሚችሉት ከጋምቤላ ዲስትሪክት ጋር አስቀድመው ቀጠሮ በመያዝ ይሆናል።
10. ለተጨማሪ መረጃ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር +251 475 512 577 / +251 475 512 588 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
11. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-09-03
- Bid closing time: 12:00
- Bid opening: 2026-09-03 12:00
- Region: Gambela
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 11, 2026)
- Posted at: 2026-08-11T10:58:36.000Z