Equipment and Accessories

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአርሲ ዞን የሁሩታ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በከተማው ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁ-01/2019

በ2019 የበጀት ዓመት በከተማው ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፤ፈርኒቸር፤ የጽህፈት መሣሪያዎች፤ የጽዳት እቃዎች፤ የሠራተኞች የደንብ ልብስ፤ እና የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

1. ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ የግብር ከፉይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ እና በፌደራል፤ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ለጽህፈት መሣሪያዎች እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ)፤ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች፤ ለጽዳት እቃዎች፤ እና ለደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ) ሁሩታ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ስም የሲንቄ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1071416861211 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዥ፤ ንብረት አስተዳደር፤ ማስወገድና ጠቅላላ አገ/ ቢሮ ቁጥር 08 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢውመ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጽ/ቤቱ የስብሳባ አዳራሽ ይከፈታል።

5. ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ለጽህፈት መሣሪያዎች ፤ እና ለመኪና ጎማዎች ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10000.00 (አስር ሺህ)፤ ለደንብ ልብስ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10000.00 (አስር ሺህ) እንዲሁም፤ ለጽዳት እቃዎች እና ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10000.00 (አስር ሺህ)፤ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ ማቅረብ አለባቸው።

6. አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ በሁሩታ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የሁሩታ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።

7. መስራያ ቤቱ ለሚፈፅማቻው ግዥውን አሸናፊው ከVAT withholding/7.5% እና TOT 3% ቆርጦ በማስቀረት ከመስራቤታችን ሕጋዊ ደረሰኝ ይሰጠዋል።

8. ተጫራቾች አስቀድመው የእቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9. አሸናፊው ተጫራቾች ቋሚ የቢሮ ፈርኒቸሮችን ገጣጥሞ፣ ለያንዳንዱ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች serial no. አስመዝግቦ በጥራት ገቢ ካደረገ በኋላ ክፍያ ይፈፀምለታል።

10. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁጥር 0952 584 048 = 0912 250 052= 0916 912 592 ይጠይቁ።

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በአርሲ ዞን የሁሩታ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-28
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-28 14:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Huruta City Administration FEDB
  • Bid bond: 10,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
  • Bid document price: 400.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 11, 2026)
  • Posted at: 2026-08-11T11:13:36.000Z
← Back to all tenders