Printing and Publishing
የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ዕቃዎች እና አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች ለመፈጸም ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ወዞፋ/ግ/01/2019
የወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞን ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ከዚህ በታች በሎት የተጠቀሱ ዕቃዎች እና አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች ለመፈጸም ይፈልጋል።
|
ሎት |
የሚገዛው ዕቃ |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
የህትመት አገልግሎት ግዥ |
60,000 |
|
2 |
የባህል አልባሳት ግዥ |
60,000 |
|
3 |
የመስተንግዶ አገልግሎት ግዥ |
60,000 |
|
4 |
የዘመናዊ ሙዚቃ መሣሪያ ከነሙሉ አክሰሰሪ ግዥ |
60,000 |
|
5 |
ድሮን ግዥ |
60,000 |
ስለዚህ ተጫራቾች፡-
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፊኬት፣ የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ (ቲን) ሰርተፊኬት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ወይም (e-GP) ማቅረብ አለባቸው።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ እና የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሠነድ እየከፈሉ ከወላይታ ዞን ፋይ/ፕ/ል/መምሪያ 2ኛ ፎቅ ከቢሮ ቁጥር 3 ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የአንዱን ዕቃ ወይም አገልግሎት ግዥ ዋጋ የሚያቀርቡበትን የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን በጨረታ ሰነድ ላይ በተዘጋጀው ዋጋ መሙያ በመሙላት በታሸገ ፖስታ በወላይታ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን በጨረታ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 19 መክተት ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውን ሰነድ 1 ኦሪጅናል እና 1 የኦርጅናሉን ፎቶ ኮፒ ለብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ሙሉ አድራሻቸውን በመጥቀስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል።
5. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመምሪያው የጨረታ አዳራሽ ይከፈታል። 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
6. አሸናፊ ድርጅት አስፈላጊውን ውለታ በመፈጸም ዕቃውን ሙሉ በሙሉ ወላይታ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ድረስ በማቅረብ ገቢ ሲያደርግ ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል።
7. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 551 2116 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ወላይታ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-08-26
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-26 14:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ8፡30 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Wolita Zone Finance and Economy Development Department
- Bid bond: በየሎቱ 60,000 ብር
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Aug 11, 2026)
- Posted at: 2026-08-11T11:36:34.000Z