Stationery

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ አላቂና ቋሚ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማስራት ይፈልጋል

Description

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ

  • አላቂና ቋሚ የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ፣
  • የኤሌክትሮኒክስና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ፣
  • የቢሮ መገልገያ እቃዎች /ፈርኒቸር/ ግዥ ፣
  • የመኪና መለዋወጫ እቃዎች የአንድ ዓመት የኮንትራት አቅርቦት ግዥ፣
  • የመኪና ጥገና የአንድ ዓመት ኮንትራት አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማስራት ይፈልጋል።

1. ዘመኑ የየታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣

2. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

3. ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ሰነዱን ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ማግኘት ይቻላል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ አላቂና ቋሚ የጽህፈት መሳሪያዎች 60000 /ስልሳ ሺህ ብር/፣ የኤሌክትሮኒክስና ተዛማጅ እቃዎች ግዥ 55,000 ሃምሳ አምስት ሺህ ብር/ የቢሮ መገልገያ እቃዎች /ፈርኒቸር) ግዥ 50000 /ሃምሳ ሺህ ብር፣የመኪና ጎማ ግዥ 40000 /አርባ ሺህ ብር፣ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች የአንድ አመት የኮንትራት አቅርቦት ግዥ 50000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ የመኪና ጥገና የአንድ አመት ኮንትራት አገልግሎት ግዥ 50,000 / ሃምሳ ሽህ ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ ፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ መሂ ማስያዝ አለባቸው።

5. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥና ንብረት አስተዳዳር ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4:30 ይከፈታል ። ሁሉም ጨረታዎች ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ይከፈታል።

6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ማሻሻያ ወይም ማብራሪያ ካላቸዉ ለዕቃና አገልግሎት ግዥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 /አስር/ ቀናት ለግ/ንብ/አስ/ቡድን በፅሁፍ ማቅረብ ይችላሉ።

7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ድረስ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 0116250146 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

9. የጨረታ መዝጊያው ቀን እሁድና ቅዳሜ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን 4፡00 ሰአት ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።

አድራሻ፡- አማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከደብረ ብርሃን 72 ኪሎ ሜትር ወደ ደሴ መስመር ከሚወስደው መንገድ ጣርማበር /ዋሻ/ ወደ ምዕራብ 22 ኪሎ ሜትር ገባ ብሎ።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን

ሸዋ ዞን የሞጃና ወደራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-26
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-26 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን በአየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: North Showa Zone Moja And Wedera Wereda Finance Economic Cooperative Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ ሰነድ 400 /አራት መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Aug 11, 2026)
  • Posted at: 2026-08-11T11:52:50.000Z
← Back to all tenders