Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በአርሲ ዞን ሸነን ኮሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳዉ ለሚገኙ መስሪያ ቤቶች የፅፈት መሣሪያ፣ የፅዳት ዕቃ፣ የደንብ ልብስና ልብስ ስፌት፣ የህትመት ሥራ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣ የቢሮ ዕቃና የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በአርሲ ዞን ሸነን ኮሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳዉ ለሚገኙ መስሪያ ቤቶች የፅፈት መሣሪያ፣ የፅዳት ዕቃ ፣የደንብ ልብስና ልብስ ስፌት፣ የህትመት ሥራ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣ የቢሮ ዕቃና የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. ለተጠየቁት የፅፈት መሣሪያ ፣የፅዳት ዕቃ ፣የደንብ ልብስ፣የህትመት ሥራ ፣የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣ የቢሮ ዕቃና የመኪና ጎማ ግዥ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር ከፍለዉ ንግድ ፈቃዳቸዉን ያሳደሱ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይነት መለያቁጥር /Tax Payer Registration No. ያላቸዉ ና በፌዴራል ፤በክልል ፤በዞን ወይም በወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ የሥራ ሂደት የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸዉ ዋናዉንና ኮፒዉን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች ለዚህ ግዥ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ለሸነን ኮሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000416995617 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከወረዳዉ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ የሥራ ሂደት ድረስ በመቅረብ መዉሰድ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ከገቢዎች መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀዉ መክፈላቸዉን የሚያሳይና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸዉን ደብዳቤ ማቅረብ የኖርባቸዋል።
4. ማንኛዉም ተጫራች በተደራጀበት ሥራ ፍቃድ ማለትም የፅህፈት መሣሪያ ፣የፅዳት ዕቃ ፣የደንብ ልብስ፣ የህትመት ሥራ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ፣ የቢሮ ዕቃና የመኪና ዕቃዎች ላይ በግሉ እንጂ በተወካይ የሚወዳደሩትን ጨረታዉን ያወጣ ሸነን ኮሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን።
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ግዝተዉ ሞልተዉ በዝግ ፖስታ ማቅረብ የሚችሉት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት ሲሆን በ16ኛዉ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ገብቶ ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች በተገኙበት በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ የሥራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል።
6. ማንኛውም ተጫራች ለዚህ ሰነድ ማስከበሪያ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ለጽህፈት መሣሪያ፣ 2000 (ሁለት ሺህ ብር) ለጽዳት መሣሪያ ፣5000 (አምስት ሺህ ብር) ለደንብ ልብስ ፣ 3000 (ሶስት ሺህ ብር) ለህትመት ሥራ፣ 10000 /አስር ሺህ ብር/ ለኤሌክትሮኒክስ፣ 10000/አስር ሺህ ብር/ ለቢሮ ዕቃ እና 5000 / አምስት ሺህ ብር ለመኪና ዕቃ ) በአቅራቢያቸው በሚገኝ የታወቀ ባንከ በከፍያ ማዘዣ (C.P.O.) ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. አሸናፊው ተጫራችየሚያቀርቡትን የእቃ ሞዴል በቅድሚያ ማስገባት እንዲሁም ያለምንም የአቅርቦት ችግር በራሱ የጭነት መኪና ሸነን ኮሉ ወረዳ ገንዘብ ቢሮ ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።
8. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር (0922646087 )0930724101) ይጠይቁ።
በአርሲ ዞን የሸነን ኮሉ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-28
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-28 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ የስራ ቀን 4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Arsi Zone Shenen Kolu woreda Finance and Economic Development Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 11, 2026)
- Posted at: 2026-08-11T12:13:20.000Z