Textile, Garments and Uniforms

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጉጂ ዞን የአና ሶራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጉጂ ዞን የአና ሶራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት የደንብ ልብስ፤ አላቂ የቢሮ እቃዎች፤ የመኪና ጎማዎች፤ ጀኔሬተሮች፤ የግብርና ግብዓቶች እና መገልገያ እቃዎች፤ ሞተር ሣይክል፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ የቢሮ ቋሚ እቃዎች፣ የቴክኒክ ሙያ ኮሌጅ እቃዎች፣ እና የግንባታ እቃዎች፣ የትምህርት መሣሪያ እና የተለያዩ ኅትመቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡

1. ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና በመንግሥት አቅራቢዎች ኤጀንሲ ውስጥ የተመዘገቡ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

2. የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ TIN Number ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡

4, በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለው፡፡

5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ6፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት 7፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡

6.ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ 2% በኢትዮጵያ ውስጥ እውቅና ባላቸው ባንኮች በተረጋገጠ ኦሪጂናል ሲፒኦ ወይም በካሽ ከጨረታ ሰነድ ጋር አብሮ ማስገባት አለባቸው፡፡

7. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ዘወትር በሥራ ቀን የማይመለስ ብር 800 (ስምንት መቶ) በመክፈል ሰነዱን ከአና ሶራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይችላሉ፡፡

8.ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ቫት በመጨመር በገዙት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በግልጽ በመሙላት እንዲሁም በመጨረሻ ስም፤ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማኖር ኮፒና ኦሪጂናሉን በመለየት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በመለየት ፖስታው ላይ በግልጽ መለየት አለበት፡፡

10. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የሚያበቃ የድጋፍ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

11. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ/መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ - 09 11 94 96 22/0911251308
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጉጂ ዞን የአና ሶራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-29
  • Bid closing time: 12:30
  • Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው የሥራ ቀን 6፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-29 13:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው የሥራ ቀን 7፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Guji Zone Ana Sora Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: ለእያንዳንዱ ጨረታ 2%
  • Bid document price: 800 (ስምንት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 12, 2026)
  • Posted at: 2026-08-12T07:33:36.000Z
← Back to all tenders