Cleaning and Janitorial Equipment and Service
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የባቢሌ ከተማ አስተዳደር የገንዘብ ጽሕፈት ቤት በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የባቢሌ ከተማ አስተዳደር የገንዘብ ጽሕፈት ቤት በ2019 በጀት ዓመት ለሁሉም የመንግሥት ጽሕፈት ቤቶች እና የከተማው ቀበሌዎች የሚሆኑ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሚገዙ ዕቃዎች
- ደንብ ልብስ
- የጽዳት ዕቃዎች የጽሕፈት መሣሪያዎች (Stationery)
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- የፈርኒቸር ዕቃዎች
- ለቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ሥልጠና የሚሆኑ ዕቃዎች
- የተሽከርካሪና የሞተር ብስከሌት መለዋወጫዎች
የጨረታ መስፈርቶች
1. ተወዳዳሪዎች የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የፋርኒቸርና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን የሚገልጽ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።
2. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት (Supplier Registration Certificate) ማቅረብ አለባቸው።
3. ከገቢዎች ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ የግብር ክሊራንስ (Tax Clearance) ማቅረብ አለባቸው።
4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
5. ተወዳዳሪዎች በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ለጠቅላላው ሰነድ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ማቅረብ አለባቸው።
6. ተወዳዳሪዎች ዕቃዎቹን የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አሥራ አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ) በመክፈል ከባቢሌ ከተማአስተዳደር ገንዘብ ጽሕፈት ቤት መግዛት ይችላሉ።
7. ተወዳዳሪዎች የተወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ዋናውን (Original) እና ፎቶ ኮፒውን በመለየትና በሰም በማሸግ በባቢሌ ከተማ ገንዘብ ጽሕፈት ቤት ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
8. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ዕቃ በገባው ውል መሠረት በራሱ ትራንስፖርት እስከ ባቢሌ ከተማ ገንዘብ ጽሕፈት ቤት ድረስ ማቅረብ አለበት።
9. ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በማስታወቂያው ላይ የተጠቀሱትን፡ የኮምፒውተር እስክሪብቶ፣ የኮምፒውተር ወረቀት፣ የፎቶ ኮፒ እስክሪብቶ፣ የሥራ ልብስ እና ለሴት ሠራተኞች የሚሰጥ ጫማ አንድ አንድ ናሙና (Sample) ማቅረብ አለባቸው።
10. የጨረታ ሰነዱ የተሰረዘና ስህተት ያለበት ከሆነ ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
11. የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
12. ተወዳዳሪዎች በሰነዱ ገጾች ሁሉ ላይ ማኅተምና ፊርማ ማድረግ አለባቸው።
13. ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡት ዕቃ በሀገር ውስጥ የጥራት ደረጃ የተረጋገጠ መሆን አለበት።
14.ተወዳዳሪው ከዚህ ቀደም በመንግሥት ግዥዎች እንዳይሳተፍ ያልተከለከለ መሆኑን የሚያስረዳ መረጃ ከመንግሥት ንብረት ማስወገድና ግዥ ኤጀንሲ ማቅረብ ወይም በዌብሳይት የተረጋገጠ መሆን አለበት።
15. ጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
16.ጽሕፈት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ፦ በስልክ ቁጥር፦0921845053 /0914947011 በሥራ ሰዓት ይደውሉ።
የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን የባቢሌ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽሕፈት ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-28
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አሥራ አምስት) የሥራ ቀናት
- Bid opening: 2026-08-28 17:00
- Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
- Region: Oromia
- Publishing entity: Babile Woreda Finance and Economic Development Office
- Bid bond: 30,000.00 ብር
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Aug 12, 2026)
- Posted at: 2026-08-12T08:34:15.000Z