Cleaning and Janitorial Equipment and Service
የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳዉ ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች የተለያዩ ዕቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳዉ ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች
- የጽህፈት መሳሪያዎች፣
- አላቂ እቃዎች፣
- ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣
- የኤሌከትሮኒክስ እቃዎች
- የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎች፣
- የተለያዩ የህትመት ዉጤቶች፣
- የ1ኛ እና የ2ኛ ደረጃ የተማሪዎች ካርድ ህትመቶች፣
- የደንብ ልብስ፣
- የሞተር ሳይክል ግዥ
- የመኪናና የሞተር ሳይክል መለዋወጫ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በዚህ ጨረታ ላይ ለመወዳዳር ለምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸዉ።
1. 2019 ዓ.ም. ግብር የገበረና የንግድ ፈታዱን ያደሰ።
2. ቲን፤ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆነ።
3. የጨረታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ዋጋ 2% በሲፒኦ (CPO) ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ከመስሪያ ቤቱ ጋር ዉል ለመፈራረም ፍቃደኛ የሆነ።
5. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500 (አምስት መቶ) ብር ለወረዳ ገቢዎች በመክፈል ከግዥ ክፍል መግዛት የሚችል።
6. Withholding Tax (3%) ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ።
7. በማይክሮ የተደራጁ ካደራጃቸዉ አካል የዋስትና ደብዳቤ ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ከአንድ ጊዜ በላይ ለዉድድር የቀረቡ 2% ሲፒኦ ማስያዝ ይገደዳሉ።
8. በደንብ ልብስ አቅርቦት ላይ ለሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች የጨርቁን ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች ሰነዳቸዉን ዋናዉን እና ፎቶ ኮፒዉን ለይቶ በማሽን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10. ተጫራቾች ሌሎች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሰዉ ዋጋ ማቅረብ በህግ የተከለከለ ነው።
11. የመመዝገቢያ ቦታ ጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ይሆናል።
12. የመመዝገቢያ ቀን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ2 ቀን በኋላ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናቶች አየር ላይ ይቆያል። ጨረታዉ የሚዘጋዉ በ15ኛዉ ቀን በ8፡00 ተዘግቶ በዚያዉ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቹ ባሉበት ይከፈታል። ባይገኙም ሊከፈት ይችላል።
13. የጨረታዉ አሸናፊ የአሸነፈበትን እቃ በራሱ ወጭ እስከ ጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ድረስ ማቅረብ የሚችል።
14. የእቃዉ ብዛት በ20% ሊቀንስም ሊጨምርም ይችላል።
15. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 047-342-0303
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጅማ ዞን የጌራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-31
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ2 ቀን በኋላ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናቶች አየር ላይ ቆይቶ በ15ኛዉ ቀን በ8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-31 14:30
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ2 ቀን በኋላ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናቶች አየር ላይ ቆይቶ በ15ኛዉ ቀን በ8፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Jimma Zone Gera Woreda FEDB
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 12, 2026)
- Posted at: 2026-08-12T08:43:04.000Z