Stationery

በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የጣርማበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዓይነት ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ግዥ/ ንብ/አስ/001/2018

በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የጣርማበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለጣ/ወ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በመደበኛ እና በተራድኦ በጀት ከዚህ በታች በየሎቱ በዝርዝር የተጠቀሱትን ዕቃዎች እና ለአገልግሎቶችን ግዥ ለመፈፀም የሚፈልግ ሲሆነ ግዥው የሚፈጸመው በየሎቱ ዓይነት በጥቅል ሲሆን ለከፊሎቹ ዋጋ መስጠት ከውድድሩ ውጭ ያደርጋል።

  • ሎት 1 የተለያዩ ዓይነት አላቂና ቋሚ የፅህፈት መሳሪያ /የፕሪንተር ቀለም/ ግዥ ብር 20,000.00 ብር
  • ሎት 2 የመኪና ጎማ ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000.00 ብር እና
  • ሎት 3 የተለያዩ ዓይነት የእንስሳት መድሀኒት ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 15,000.00 ብር
  • ሎት 5 የተለያዩ ዓይነት የእንስሳት የህክምና ቁሳቁስ ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 ብር
  • ሎት 6 የህትመት አገልግሎት ኮንትራት ግዥ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00 ብር ማስያዝ አለባችሁ።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በየዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ ቲን ነምበር = የምታቀርቡት ዋጋ 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

1. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዝርዝር ጉዳይ የያዘ የእያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ያለውን የማይመለስ ብር በሚወዳደረበት ዘርፍ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) “ገንዘብ ጽ/ቤት በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከሎት 1 እስከ ሎት 6 በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።

2 ተጫራቾች ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ያሉት ሰነዶች በእያንዳንዱ የዋጋ ዝርዝር ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ውስጥ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋውን ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በጥንቃቄ በመሙት የድርጅቱን ማህተም ስም ፊርማ አድራሻ ስልክ ቁጥር በማስፈር ኦርጅናል የመጫረቻ ሰነድ በፖስታ አሽገው በደብረሲና ከተማ ፀደይ ባንክ ህንጻ ጣርማበር ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ሶስተኛ ፎቅ ሃላፊ ቢሮ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባችኋል። ከሎት 1 እስከ ሎት 6 የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ ከሎት 1 እስከ ሎት 6 በአዲስ ዘመን በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጧቱ 4:29 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፣ የጨረታው ሳጥኑ 4፡30 ሰዓት ይታሽግና በዚሁ ቀን 4፡45 የሚከፈት ሲሆን ቀኖቹ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀን ይከፈታል።

3. ነጠላ ዋጋውና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ልዩነት ካለ የነጠላ ዋጋው ተቀባይነት ይኖረዋል፣፣

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው ከታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደ ተጫራቾች ምርጫ ሲፒአ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም ለመስሪያቤቱ ዋና ገንዘብ ያዥ በመሂ በጥሬ ገንዘብ በምትወዳደሩበት ከላይ በየሎቱ ለተጠቀሱት ዘርፍ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማሽን ማስያዝ ይጠበቀባችዋል።

5. ተጫራቾች አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።

6. አሸናፊው ተጫራች ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ግዥ በጣ/ወ/ሲና ከተማ በ4ም ፑል ንብረት ከፍል ድረስ በማቅረብ በባለሙያ እየተረጋገጠ በስሙ ገዢ ማድርግ አለባቸው።

7. መስሪያቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. ለይበልጥ ማብራሪያ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ከተያዘው የተጫራቾች መመሪያ በማንበብ መረዳት ይችላሉ።

9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116800432/0116800068/ ደውለው ይጠይቁ።

በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን የጣርማበር ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-27
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጧቱ 4:30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-27 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጧቱ 4:45 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Tarmaber Woreda FEDB
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 12, 2026)
  • Posted at: 2026-08-12T08:59:20.000Z
← Back to all tenders