Stationery
በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ወለጋ ዞን የነጆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ወለጋ ዞን የነጆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ
- ሎት፡-1የጽሕፈት፤ የጽዳትና የተለያዩ ዕቃዎች
- ሎት2፤ የኤሌክትሮኒክስ እና የቢሮ ፊርኒቸሮች
- ሎት3፤ የተለያዩ ጎማዎች እና የመ/ ሠራተኛች ደንብ ልብስ
- ሎት4፤ የግንባታ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ሰለ ጨረታው የሚገልጽ ዝርዝር ሰነድ ለእያንዳዳቸው ሎቶች የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት በነጆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቀርባችሁ መግዛት የምትችሉ ሲሆን፤
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
1. ተጫራቾች የዓመቱ የታደሰና ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና ከሚመለከተው መ/ቤት የተመዘገቡበትን የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ
2. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ለሁሉም ሎቶች ለእያንዳዳቸው ብር 20,000 (ሃያ ሺህ) ሲሆን ለሎት3 ብር 10,000 (አሥር ሺህ) ከሚያቀርቡት ጨረታ ሰነድ ጋር ማሰያዝ አለባቸው፡፡
3. የጨረታ ተሳታፊዎች የሚያቀርቡትን ጨረታ የቴክኒክ ሰነድ ዋናውን እና የፋይናንስ ሰነድ ዋናውን ለየብቻ ታሽጎ በፖሰታ በማድረግ ይህ ማሰታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት በሥራ ሰዓት ከ2፡30-11፡30 ድረሰ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማሰገባት አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ጋር መሆኑን መግለጽ አለባቸው፡፡
5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን በ5፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በነጆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ቀኑ በዓል ወይም የእረፍት ቀን ላይ ከዋለ በቀጣይ በሥራ ቀናት በተመሳሳይ ሁኔታ ታሸጎ ይከፈታል፡፡
6. በገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አካላት በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የዕቃ ስምና (Brand Name) የተመረተበትን ሀገር መግለጽ ይኖርባቸዋል።
8. የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው ዝርዝር መሠረት ተሟልተው ካላቀረቡና ማንኛውንም ዓይነት ስህተት ቢፈጽም ሀላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ነው፡፡
9. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ጥራቱን የጠበቀ መሆን አለበት፡፡ ጥራቱን ያልጠበቀ ዕቃ ካቀረቡ ይዘው ይመለሳሉ፡፡
10. ማንኛውንም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም፡፡
11. መ/ቤታችን የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት እንደአስፈላጊነታቸው በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይቻላል፡፡
12. ተጫራቾች በጨረታው ተካፋይ ለመሆን የሚፈልጉት ለምን ለምን ዓይነት ዕቃ አንደሆነ በሰነዳቸው ላይ በትክክል ለይተው መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡
13. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን ዕቃዎች ውል ይፈራረማሉ ውሉ እንደአስፈላጊነቱ እስከ በጀት ዓመቱ መጨረሻ የሚቆይ ይሆናል፡፡
14. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
15. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መጻፍ አለበት፡፡
16. ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ የመቆያ ጊዜ ጨርሰው መክፈቻ ዕለት ጀምሮ የሚጸናበትን ጊዜና ሥራውን አጠናቀው የሚያስረክቡት ጊዜ መግለጽ አለባቸው፡፡
17. አንድ ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ (መፈጸም አይችልም፡፡
18. የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታው አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደተገለጸ አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ ገንዘብ 10% በማስያዝ በነጆ ወረዳ ገንዘብ ጽ /ቤት መጥተው ውል መፈራረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈጸም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ የጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
19. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸው ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት በነጆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
20. የእቃዎችን ዋጋ የምንከፍለው ዕቃዎቹ በግምጃ ቤታችን ገቢ ከሆኑ በኋላ ይሆናል፡፡ ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከሥር በምንረከበው ዕቃ መጠን ወይም ብዛት ልክ ክፍያ መፈጸም ይቻላል፡፡
21. በወቅቱ ያልቀረበ የጨረታ ሰነድ ፤ከጨረታ ሳጥን ውጭ የተገኘ የጨረታ ሰነድ፤ የባለቤትነት ወይም የሕጋዊ ተወካይ ማስረጃ የሌለው ተጫራች ተቀባይነት የለውም፡፡
22. በጨረታ ሰነድ ውስጥ ያልተቀመጠ መስፈርት ለግምገማ አያገለግልም፡፡ ጨረታው ሲከፈት ሁከት ማንሳት የተከለከለ ነው፡፡
23. ተጫራቾች ለሚጫረቱት ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
24. ሁሉም ተጫራቾች በየንግድ ዘርፉ የመሳተፍ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
25. ለጨረታው ማሰከበሪያ የተያዘ CPO ተመላሸ የሚሆነው አሸናፊ ድርጅት ከተገለተጸ በኋላ ነው፡፡
26. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0577740108/13 እና 0917817733 ወይም
0913554324 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ወለጋ ዞን የነጆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-01
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን በ5፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-01 14:00
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Nejo Woreda FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Aug 12, 2026)
- Posted at: 2026-08-12T09:05:15.000Z