Software Provision, Development and Web Design
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባለው በጀት የሶፍትዌር ፈቃዶች፣ የክላውድ (Couch) አገልግሎቶች እና የደህንነት ሶፍትዌር አማራጮች ግዥ (Procurement of Software Licenses Cloud Services and Security Solution) ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፦ ECMA/NCB/OB/01/2019
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ባለው በጀት የሶፍትዌር ፈቃዶች፣ የክላውድ (Couch) አገልግሎቶች እና የደህንነት ሶፍትዌር አማራጮች ግዥ (Procurement of Software Licenses Cloud Services and Security Solution) ግዥ በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፣
1 በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን እና ሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ቀን ድረስ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመ/ቤታችን አካውንት 1000586364824 ገቢ በማድረግ ከባለስልጣኑ ፋይናንስና ግዥ ክፍል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
2- ተጫራቾች የመወዳደርያ ሰነዳቸውን ፋይናንስና ቴክኒካል ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
3- ተጫራቾች በዘርፉ ያላቸውን በዘመኑ የታደስ ንግድ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የግብር ክሊራንስ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረገጽ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን እንዲሁም የተፈረመና ማህተም ያለው የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የተገባበት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
4. ተጫራቾች ዋጋቸውን በመሙላት ባለስልጣኑ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡና ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
5- ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው 15 ቀናት ብቻ ነው፡፡
6 ተጫራቾች በሚያቀርቧቸው ሰነዶች ላይ የድርጅታቸውን ማህተምና የተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪል ፊርማ መኖር ይገባዋል።
7. አሸናፊው ተጫራች አገልግሎቱ በተፈለገ ጊዜ አገልግሎቱን የመስጠት ኃላፊነት አለበት፡፡
8- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያነት የብር 60,000.00 (ስልሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም ሲፒኦ/ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
9- ተጫራቾች የቀረበውን ዝርዝር መስፈርት መሰረት በማድረግ የሚያቀርቡትን አገልግሎት ዝርዝር የቴክኒክ መግለጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
10- አንዱ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
11- ጨረታው ነሃሴ 20 ቀን 2018 ከሰዓት 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከሰዓት በ4:30 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባለስልጣኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
12- በጨረታው መክፈቻ ዕለት የተጫራቾች አለመኖር ጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም፡፡
13- ባለስልጣኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ አካል የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን አድራሻ ቦሌ መንገድ ፍላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ ባለው ዋ/መ/ቤት በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ።
የፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት
ከፍላሚንጎ ሪስቶራንት ወደ አደራ ሆስፒታል በሚወስደው መንገድ ምናዬ ህንፃ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ስልክ 011-5-57-83-27
ኢሜል: Procurementeta.gov.et
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን
Tender details
- Deadline: 2026-08-26
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-08-26 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Capital Market
- Bid bond: 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር)
- Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 12, 2026)
- Posted at: 2026-08-12T09:14:11.000Z