Equipment and Accessories
በአርሲ ዞን የጀጁ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሣሪያዎች እና የሠራተኞች ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and Accessories
Oromia
Description
1ኛ. የጨረታ ማስታወቂያ ቁ- C1-01/2019
በአርሲ ዞን የጀጁ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳ ለሚገኙ የመንግስት መሥራቤቶችና የቀበሌ አስተዳደሮች አገልግሎት የሚውሉ
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ኤሌክትሮኒክስ፣
- ፈርኒቸር፣
- የጽህፈት መሣሪያዎች፣
- እና የሠራተኞች ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-
- ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No. ) የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና በፌዴራል በክልል ወይም በዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ወይም በግዥዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ አቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፤ ለጽህፈት መሣሪያዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500(አምስት መቶ) ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች እና ለደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 400(አራት መቶ) በጀጁ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000075254591 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዥ፤ንብረት አስተዳደር፤ማስወገድና ጠቅላላ አገ/ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለሚገኙ ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ጨረታው በ 16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ 5፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጽ/ቤቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፤ ለፈርኒቸር እቃዎች እና ለጽህፈት መሣሪያዎች ሰነድ ለእያንዳንዱ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 40,000( አርባ ሺህ) ለደንብ ልብስ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25,000 (ሃያ አምስት ሺህ) በአቅራቢያቸው በሚገኝ የታወቀ ባንክ በክፍያ ማስያዥያ (CPO ) ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
- አሸናፊው ተጫራችያለምንም የአቅርቦትችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ አርቦዬ ከተማ ውስጥ በሚገኘው በጃጁ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 0919216098 ፤ 0921469938 ፣ 0916522762 ይጠይቁ።
በአርሲ ዞን የጀጁ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-29
- Bid closing time: 11:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 5፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-29 11:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 5፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Arsi Zone Jeju Woreda FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Published on: Addis Zemen (Aug 12, 2026)
- Posted at: 2026-08-12T10:59:29.000Z